ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ለኢየሩሳሌም የእሥራኤል መዲናነት ዕውቅና በመቸር ለአሠርት ዓመታት የነበረውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ፖሊሲ ቀይረዋል። አቶ ትራምፕ ውሳኔው ከቶውንም ሊከወን ይገባ የነበረው ከረጅም ጊዜያት በፊት እንደነበርና ከእሳቸው በፊት የነበሩት መሪዎች ግና ይህን ማድረግ የተሳናቸው መሆኑን ገልጠዋል። ለውሳኔያቸው የተሰነዘሩት አጸፋዎች ግና እጅጉን ፈጣንና የሚጠበቁም ነበሩ።
Share






