Watch FIFA World Cup 2026™ LIVE, FREE and EXCLUSIVE

Life and Legacy: Prof Getachew Haile – Pt 2

Life and Legacy: Prof Getachew Haile – Pt 2

Prof Getachew Haile Source: Courtesy of GH and PD

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ በመንፈሳዊና ዓለማዊ ዕውቀት ተጠባቢነት ለሊቀ ሊቃውንትነት የበቁ ናቸው። የዕውቀት ጭማቂያቸውን ከደርዘን በላይ ለሕትመት በበቁ መጻሕፍቶቻቸው ላይ አስፍረዋል። ለበርካታ ማለፊያ አስተዋጽዖዎቻቸውም ከኢትዮጵያውያንና ከውጭ አገር ድርጅቶች ከግማሽ ደርዘን ያለፉ የክብር ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል። በክፍል ፪ ዝግጅታችን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤ እንደምን ወደ ሴማዊ ጥናቶች ተስበው ለሕይወት ጥሪ ምላሽ እንዳፈላለጉ፣ የነጻ የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደ አገረ ጀርመን እንደዘለቁ አንስተው ያወጋሉ።


እንደወጡ አልቀሩም፤ ከ፲፩ ዓመታት የግብጽና ጀርመን የአፍላ ወጣትነት የትምህርት ጥማት እርካታ በኋላ ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

Life and Legacy: Prof Getachew Haile – Pt 2
ፊርማ የሚጠይቁ ወጣቶች - 'አንዳፍታ ላውጋችሁ' ጌታቸው ኃይሌ Source: Courtesy of GH

ሕልማቸው የባህር ማዶ ዕውቀትን በመምህርነት ለአገር ዕድገት ማዋል ነበርና ቀድመው ያመሩት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ነበር። ወቅታዊ ምላሽ ሳያገኙ ቀሩ። ተስፋ አልቆረጡም። ይልቁንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የነበሩት የዶ/ር አክሊሉ ኃብቴን ቢሮ በር አንኳኩ። ፕሬዚደንቱ በአንድ እጃቸው በራቸውን ገርበብ አድርገው ከፍተው በሌላ እጃቸው ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መንገድ አመላከቷቸው።

እንደተባሉት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቀኑ። ሚኒስትር ከተማ ይፍሩን አነጋገሩ። አቶ ከተማም የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ የሚከውንላቸው የተማረ ሰው ይፈልጉ ነበርና ‘ለምን አታግዘኝም?’ ብለው ጠየቁ።

የዶ/ር ጌታቸው ምላሽ እሺታ ሆነ። ክረምቱን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛነት አሳለፉ። ክረምቱ በበጋ ሲተካ፤ በዶ/ር አክሊሉ ኃብቴ በኩል የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ጥናት ክፍል አስተማሪ እንደሚፈልግ ተጠቆሙ።

ውስጣቸው ተቀብሮ የነበረው የአስተማሪነት መንፈስ ገንፍሎ ወጣ። የልጅነት ምኞታቸውን ዕውን ለማድረግ ውጭ ጉዳይን ጥለው ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እብስ አሉ። መንበራቸውን ዘርግተው ማስተማር ጀመሩ።

በአስተማሪነቱ ጥቂት ጊዜያትን እንደገፉ በድንገት ከግቢ ጥሪ ደርሳቸው። ንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ቀረቡ። በቤተክህነት አስተዳዳሪነት መሾማቸው ተነገራቸው። ቅሬታቸውን በልባቸው ይዘው እጅ ነስተው ወጡ።

Life and Legacy: Prof Getachew Haile – Pt 2
'አንዳፍታ ላውጋችሁ' ጌታቸው ኃይሌ Source: Courtesy of GH

ከግቢ እንደወጡ ገስግሰው የሄዱት ወደ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዘንድ ነበር። ከመምህርነት ወደ አስተዳዳሪነት እንደምን ሊሾሙ እንደበቁ ለመጠየቅ። የተሰጣቸው ምላሽ ግና አላረካቸውም።

እናም፤ የሌላ ቅሬታ ሰሚ በር ማንኳኳት ግድ ሆነ። ለሹመት ያቀረቧቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ፊት ቀረቡ። ብቃትና ውዴታቸው ማስተማር እንጂ ማስተዳደር አለመሆኑን አዋዝተው ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተዋዝቶ የቀረበው ቅሬታ ገብቷቸው ከሳቅ ጋር በብቃትና ውዴታቸው እንዲሰሩ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ሰጥተው ሸኟቸው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በግብር ዋለ።


Share

Follow SBS Amharic

Download our apps

Listen to our podcasts

Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now