ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ከቆዩ ግማሽ ያህል የአውስትራሊያ ተማሪዎች ወደ ኋላ ሊቀሩ ይችላሉ የሚል ሥጋት አድሯል

** ስፔይን ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚ የፊት ጭምብል እንዲለብስ ደነገገች

0800 core bulletin 3 May

Source: Getty Images

ቫይረስ - ትምህርት ቤቶች

 

 አንድ አዲስ የወጣ ሪፖርት የአውስትራሊያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ከቆዩ ተማሪዎች በትምህርታቸው ወደ ኋላ እንደሚቀሩ አመለከተ።

ግኝቱ እንደጠቆመው ከቤት ሆኖ ትምህርትን መከታተሉ ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎች በቂ ድጋፍ ካላገኙ ወደ አሽቆለቆለ ውጤት ሊመራቸው እንደሚችል አሳስቧል።

ሪፖርቱ ይፋ የሆነው የመንግሥት አማካሪ የሆነውና ዋና ሳይንቲስት አለን ፊንክሊ በሊቀመንበርነት የሚመሩት ፈጣን የመረጃ ግብረ ምላሽ ፎረም ነው።

የምርምሩ ትንታኔ የተካሔደው የኦንላይን ትምህርትን ከመማሪያ ክፍል ትምህርት ጋር ያነጻጸሩ 35 ድርጅቶች ጥናቶች ላይ ነው። ሪፖርቱ ለትምህርት ሚኒስትር ዳን ቲሃን ቀርቧል።  

                                                         ቫይረስ - ስፔይን 

 

የስፔይን መንግሥት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ከሰኞ ጀምሮ ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት ተገልጋይ ግለሰብ የፊት ጭምብል እንዲያጠልቅ ድንጋጌ አውጥቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ሁሉም አገሪቷ ያስቀመጠቻቸው መስፈርቶች ካልተሟሉ በስተቀር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር እንደማይቻል ዜጎችን ልብ አሰኝተዋል። 

 

ከሰኞ ጀምሮ ሸማቾች ፈጣን ምግቦችን ከቤት ወጥተው መግዛት፣ በነጠላ ሆነው ወደ ችርቻሮ ሱቆችና የጸጉር ሳሎኖች መሔድ ተፈቀዶላቸዋል።

ከቅዳሜ ጀምሮም ስፔናያውያን ከቤት ውጪ የአካል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይችላሉ። 

ስፔይን 25 000 ሰዎቿን በኮሮናቫይረስ በማጣቷ ጥብቅ የኮቪድ - 19 ገደቦች ከጣሉት አገራት አንዷ ናት። 

                                                     

 

ቫይረስ - አውስትራሊያ 

 

 አውስትራሊያ ውስጥ ትናንት ቅዳሜ 16 አዲስ በኮቪድ - 19 የተያዙ ሰዎች በመገኘታቸው ጠቅላላ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ 6783 ከፍ ብሏል።

የሟቾች ቁጥር 93 ላይ ረግቷል።

5789 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

እስካሁን 611,000 አውስትራሊያውን የኮሮናቫይረስ ምርመራ አካሂደዋል።

  

                                                         ቫይረስ - ታዝማኒያ

ታዝማኒያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በብርቱ ትባትልበት በነበረው ሰሜን - ምዕራብ ክፍሏ ጥላቸው የነበሩት ገደቦች ከሰኞ ጀምሮ ይረግባሉ።

የስቴት የጤና ባለ ሥልጣናት ቅዳሜ ዕለት አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው እንደሌለ አስታውቀዋል።

ፕሪሚየር ፒተር ገትዊን ኮቪድ - 19ኝን ለመቆጣጠር ታዝማኒያ መልካም ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል። 

 

                ቫይረስ - አፕ

 

 የአውስትራሊያ ምክትል የጤና ኃላፊ ከአራት ሚሊየን በላይ አውስትራሊያውያን የኮቪድሴፍ አፕ ስልኮቻቸው ላይ መጫናቸውንና መረጃዎቹ ገና ለስቴትና ክፍለ ግዛታት አለመድረሳቸውን አስታውቀዋል።

 

ምክትል የጤና ኃላፊ ማይክል ኪድ የጤና ባለ ሥልጣናት ለጊዜው ዳታዎችን ለማግኘት ሂደቶቹ የተጓተቱባቸው ቢሆንም በመጪው ሳምንት እክሉ እንደሚከላ ተናግረዋል።

 

የጆንሰን ልጅ

 

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና ዕጮኛቸው ኬሪ ሲመንድስ ሰሞኑን የተወለደ ወንድ ልጃቸውን የእንግሊዙን መሪ ሲያክሙ በነበሩት ሁለት ሐኪሞች ስም ሰይመዋል።

ሕጻኑ የተወለደው ባለፈው ሳምንት ሲሆን ስሙም ዊልፍሬድ ሎውሪ ኒኮላስ ጆንሰን ሆኗል።

 አቶ ጆንሰን በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው በፅኑዕ ታምመው የነበሩ ሲሆን፤ ለማገገም ያስቻሏቸውን የሕክምና ባለ ሙያዎች ሁሉ አመስግነዋል።

 

                                            

 

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now