ዩናይትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ማስታገሻ አገኘሁ አለች

**የዓለም ጤና ድርጅት አያቶች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ከልጅ - ልጆቻቸው ጋር ጊዜያቸውን ማሳለፍ ይችሉ እንደሁ ክለሳ እያደረገ ነው

0800 CORE BULLETIN 300420

Source: Courtesy of PD

ቫይረስ - ዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት

የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ባለ ሥልጣን ፀረ ቫይራል መድኃኒቱ ሬምዲሲቪር ለኮሮናቫይረስ ሕሙማን መልካም ውጤቶችን ማስገኘቱን ገለጡ። 

 የምርምሩን ውጤት ሲከታተሉ የነበሩት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ መድኃኒቱ ኮሮናቫረስን ሊገታ እንደሚችልና ከፕላሴቦ በተሻለ 31 ፐርሰንት ፈጣን የማገገም  ውጤት ማሳየቱን ተናግረዋል።

"ሬምዲሲቨር ሕሙማንን በአማካይ በ11 ቀናት ውስጥ እንዲያገግሙ ሲያስችል ፕላሴቦ 15 ቀናትን ይወስዳል" ብለዋል። 

የመድኃኒቱ ተጠቃሚዎች ለሞት የመዳረግ ሁነት ዝቅ ያለ ቢሆንም በንፅፅሮሽ እምብዛም ለውጥ የለውም። በምርምር ሂደቱ እንደታየው የሬምዲሲቨር ተጠቃሚ ቡድን የሞት መጠን 8.0 ፐርሰንት ሲሆን የፕላሴቦ 11.6 ፐርሰንት ነው።

ሙከራው የተጀመረው ፌብሪዋሪ 21 ሲሆን፤ 1,063 ሰዎች ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ፣ አውሮፓና እስያ ከተሞች ተሳትፈውበታል።

ሬምዲሰቨር ቫይረሱን መግቻና ፈጥኖ ማገገሚያ እንጂ ፈዋሽ እንዳልሆነም ተመልክቷል።

 

ቫይረስ - ልጆች

  

የዓለም ጤና ድርጅት አያቶች ለኮሮናቫይረስ ጥቃት ሳይጋለጡ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር ጊዜያቸውን ማሳለፍ ይችሉ እንደሁ ክለሳ እያካሄደ ነው። 

አንድ የስዊዝ ጤና ባለ ሥልጣን አያቶች ለኮቪድ - 19 መዛመት አደጋ ሳይጋለጡ ከ 10 ዓመት በታች የሆኑ የልጅ ልጆቻቸው ጋር መቆየት እንደሚችሉ ምክረ ሃሳባቸውን ለግሰዋል።

 

ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው አረጋውያን ለኮሮናቫረስ ከተጋለጡ በአብዛኛው ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ አኃዞች ስለሚያመለከቱ የደኅንነታቸው ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል።  

 

 

ቫይረስ - የአረጋውያን መጦሪያ

 

 በምዕራብ ሲድኒ የሚገኘው ኒውማርች ሃውስ የአረጋውያን መጦሪያ ውስጥ አንድ ተጨማሪ አረጋዊ በትናንትናው ዕለት በኮሮናቫረስ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።

 

በትናንትናንው ዕለት ሞታቸው ከተነገረው አረጋዊ 24 ሰዓታት በፊት በኒውማርች ሃውስ መጦሪያ ውስጥ የአራት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በጥቅሉ የ12 ተጠዋሪዎች ሕይወት በኮቪድ - 19 ለሕልፈት በቅቷል።

ኒውማርች ሃውስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ አረጋውያኑ ተጠቂ መሆናቸውን ያሳወቀው ኤፕሪል 11 ሲሆን ከዚያ ወዲህ 22 ሠራተኞችና 34 ተጠዋሪዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

አውስትራሊያ ውስጥ በኮቪድ - 19 ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 90 ደርሷል።

 

 

 

                                                        

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now