ሉላዊ የኮቪድ - 19 ሞቶች 200,000 ሲደርሱ አውስትራሊያ ውስጥ 81 ደረሰ

** የቪክቶሪያ ተቃዋሚ ቡድን መሪ ተማሪዎች መማሪያ ክፍሎቻቸው ሆነው እንዲማሩ ጥሪ አቀረቡ

1100 CORE BULLETIN 26/04/20

Source: Courtesy of PD

ቫይረስ - የሞት መጠን

 

በኮቪድ - 19 በመላው ዓለም ሕይወታቸው የተቀጠፈ ሰዎች ቁጥር 200,000 ሲደርስ አውስትራሊያ ውስጥ 81 ደርሷል።

የአውስትራሊያን የሞት ቁጥር 81 ያደረሰው ለሊቱን በኒው ሳውዝ ዌይልስ የኒውማርች ሐውስ የአረጋውያን መጦሪያ ተጠዋሪ የነበሩ አንድ የ83 ዓመት አረጋዊ ለሕልፈተ ሕይወት በመዳረጋቸው ነው።

ከኒው ሳውዝ ዌይልስ የኒውማርች ሐውስ የአረጋውያን መጦሪያ ተጠዋሪዎች ውስጥ 48 ሰዎች በኮረናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ትናንት ሕይወታቸው ያለፈውን አዛውንት ጨምሮ ስድስት ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል።

 እስከ ዛሬ እሑድ ኤፕሪል 26 ማለዳ ድረስ በኮቪድ - 19 አውስትራሊያ ውስጥ 81 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ 6,703 በቫይረሱ ተይዘዋል፣ 5,387 አገግመዋል፣ 499,000 ምርመራዎች ተካሂደዋል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 16 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

በሉላዊ ደረጃ 200,000 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 2,858,489 ተይዘዋል፤ 809,923 አገግመዋል።

   

                                                         

 

ቫይረስ - ትምህርት ቤቶች

 

የቪክቶሪያ ተቃዋሚ ቡድን የኮሮናቫይረስ ወረርሽን መስፋፋት ፍርሃት መስፈንን ቢገነዘብም፤ መንግሥት ትምህርት ቤቶችን እንዲከፍት ጥሪ አድርጓል።

ቪክቶሪያ ውስጥ ትምህርት ቤቶች በይፋ ያልተዘጉ መሆኑን ተመርኩዘው የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ቤታቸው ውስጥ መማር የሚችሉ ልጆች ከቤት ውስጥ ሆነው መማራቸውን መቀጠል እንደሚችሉ አስታውቀዋል። 

ይሁንና የተቃዋሚ መሪው ማይክል ኦ'ብራያን ከጤና ባለ ሥልጣናት ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ገብተው መማር እንደሚችሉ ምክረ ሃሳብ በመሰጠቱ ትምህርታቸውን መማሪያ ክፍሎቻቸው ውስጥ ሆነው ሊማሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የቪክቶሪያ ትምህርት ሚኒስትር ጄምስ ሚርሊኖ በበኩላቸው ከሚሊየን በላይ የሆኑ ተማሪዎች፣ ወላጆችና መምህራን በአንድ ላይ በሚታደሙበት ወቅት አደገኛ የቫይረስ ወረርሽኝ ሊያስከትል እንደሚችል ከጤና ባለ ሥልጣናት ምክር በመቸሩ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከቤት ሆነው እየተከታተሉ መሆኑን ገልጠዋል። 

 

 

                                                         

 

ቫይረስ - አፕ

 

 የኮሮናቫይረስ ከያዘው ግለሰብ ጋር ከ15 ደቂቃ በላይ ወይም በቅርበት የተገናኘን ሰው የሚጠቁመው አወዛጋቢ አፕ በዛሬው ዕለት እሑድ ይፋ ይሆናል።

የሲንጋፖር ሶፍትዌርን የሚጠቀመው አፕ የብሉቱዝ ኃይልን በመጠቀም የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎችን ዳታ ለጤና ባለ ሥልጣናት ያስተላልፋል።  

መንግሥት አፑ የግል ዕለታዊ ማስታወሻን ከማገላበጥ ወይም 'የት ነበር የዋልኩት' ብሎ ለማስታወስ ከመቸገር የተሻለ መሆኑን አስገንዝቧል። 

የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ ለአፑ ሥራ ላይ መዋል ከመርህ አኳያ ድጋፍ ቢሰጥም መንግሥት የሰበሰባቸውን ዳታዎች ከቫይረስ ክትትል ባሻገር ለሌላ ጉዳይ እንዳይጠቀምባቸውና የወረረሽኙ ወቅት ሲያከትምም እንዲደለዝ ግድ የሚያሰኝ ድንጋጌ እንዲያወጣ አሳስቧል። 

 

 

 

 

 

.

 

 

 

 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now