ውጥረት ሰፍኗል - አውስትራሊያ ቻይናን ከዓለም የንግድ ድርጅት ዘንድ ለመክሰስ ግድ ልሰኝ እችላልሁ እያለች ነው

**ቪክቶሪያና ምዕራብ አውስትራሊያ ምግብ ቤቶች፣ ካፌና መጠጥ ቤቶችን ክፍት ሊያደርጉ ነው

1600 Amharic news May 17, 2020

Source: Getty Images

አውስትራሊያ - ቻይና የንግድ ውዝግብ

 የአውስትራሊያ ንግድ ሚኒስትር ሳይመን በርሚንግሃም እያደገ የመጣውን የንግድ ውጥረት ለማርገብ ከቻይናው አቻቸው ጋር በስልክ ለመነጋገር ቢጥሩም እንዳልተሳካላቸው ገልጡ።

አውስትራሊያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መነሻ አስመልክቶ ምርመራ እንዲካሄድ እየገፋች ባለችው አጀንዳ ቁጣን የተላበሰችው ቻይና፤ በአራት የእርድ ከብት ሥጋ አቅራቢ ድርጅቶች ላይ ዕገዳንና በገብስ የውጭ አቅርቦት ምርት ላይ ታሪፍ ጥላለች።

ይሁንና ሴናተር በርሚንግሃም የቻይና ዕገዳና ታሪፍ ከኮቪድ - 19 ምርመራው ጋር ተያያዥነት የለውም ባይ ናቸው። 

ሚኒስትሩ ምላሽ ባያገኙም ጥረታቸው እንደሚቀጥል ሲገልጡ፤ 

" ከቻይናው አቻዬ ጋር ለመወያየት እንድችል ጥያቄ አቅርበናል። እስካሁን ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም። የአውስትራሊያ መንግሥት የአቋም ልዩነት ያላቸውን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ ሽርካዎቹ ጋር ማስተዋል የተመላመበትና ማለፊያ ውይይት ለማድረግ ሁሌም በሩ ክፍት መሆኑን ገልጫለሁ። በአፀፋው የሁለትዮሽ ተግባቦቶችን ለማካሔድ ወይም ላለማካሔድ መወሰን ግና የእነሱ ፈንታ ነው" ብለዋል።

አክለውም፤ ምናልባትም ቻይና በዛቻዋና እርምጃዋ ከቀጠለች አውስትራሊያ ክሷን ወደ ዓለም የንግድ ድርጅት ልትወስድ እንደምትችል አሳስበዋል። 

ቻይና የአውስትራሊያ አንድ ቁጥር የንግድ ሽርካ ብትሆንም፤ ሴናተር በርሚንግሃም 'የንግድ ተቋማት ሸቀጦቻቸውንና ግልጋሎቶቻቸውን ለማን መሸጥ እንዳለባቸው መወሰን የነሱ ፈንታ ነው' ብለዋል።

 

ቫይረስ - ቪክቶሪያ

የቪክቶሪያ መንግሥት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ተጥለው የነበሩትን ገደቦች ለማላላት በወጠነው ዕቅድ መሠረት ከጁላይ 1 ጀምሮ ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶች ክፍት ይደረጋሉ። 

ማስተናገድ የሚችሉትም እስከ 20 ሰዎች ይሆናል።

በጁላይ አጋማሽ ላይም ትላልቅ አዳራሾች ያሏቸው እስከ 100 ደምበኞችን ማስተናገድ ይችላሉ።   

ቫይረስ ምዕራብ አውስትራሊያ

የምዕራብ አውስትራሊያ ፕሪሚየር ማርክ ማክጋዋን ከሰኞ ጀምሮ ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶች ዳግም ሲከፈቱ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው አሳሰቡ።

ግልጋሎት ሰጪዎቹ ከነገ ጀምሮ በአንድ ጊዜ እስከ 20 ደምበኞችን እንዲያስተናግዱ ተፈቅዶላቸዋል።   

የቪክቶሪያው ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስና ማክጋዋን ነዋሪዎቻቸው ማኅበራዊ ርቀትን ከመጠበቅ እንዳይዘናጉ አሳስበዋል።  

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now