አውስትራሊያና ቻይና በኮሮናቫይረስ መነሻ አስባብ ብርቱ ወደ ሆነ ውዝግብ እያመሩ ነው

** አውስትራሊያ ውስጥ የማኅበረሰብ ኮቪድ - 19 ተጋቦት ወደ ማክተሙ እያመራ ነው

Chinese - Australian flags

Source: AAP

ቫይረስ - ምርመራ 

 

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መነሻን አስመልክቶ ሉላዊ ምርመራ እንዲካሄድ እየገፋ ሲሆን፤ ቻይና በበኩሏ የአውስትራሊያ መንግሥት በዚህ አቋሙ ግርሮ ከገፋ ከአውስትራያ ዋነኛ የውጭ አቅርቦት ላኪዎችን ምርቶች መቀበሏን ልትገታ እንደምትችል ማስጠንቀቂያ አዘል አቋሟን አደባባይ አውላለች።

  በአውስትራሊያ የቻይና አምባሳደር አውስትራሊያ ወረርሽኙን አስመልክታ ለምትገፋው የምርመራ አጀንዳ ቻይና በአውስትራሊያ ቱሪዝም፣ ግብርናና ትምህርት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል አስጠንቅቀዋል።

ይሁንና የአውስትራሊያ የንግድ ሚኒስትር ሳይመን በርሚንግሃም አውስትራሊያ ለቻይና ዛቻ እንደማትባጅ ጠቅሰው ተናግረዋል።

አክለውም፤

"እዚህ ላይ ግልጽ እንሁን። ኮቪድ - 19 በዓለም ላይ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል፤ ሚሊዮኖችን ለሥራ አጥነት ዳርጓል፤ በቢሊየን የሚቆጠሩቱ አዘቦታዊ ሕይወታቸው ተስተጓጉሏል። ዓለም የመጨረሻ ሊያነሳ የሚገደው ነገር ቢኖር በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ ለወደፊቱ ዳግም ተመሳሳይ ክስተት እንዳይከሰት ቅድመ መከላከል ለማድረግ ይበጅ ዘንድ የኮቪድ - 19 መነሾን አስመልክቶ ግልጽ ምርመራ እንዲካሄድ መጠየቅ ነው" ብለዋል።

 

ቫይረስ - ተዛማችነት 

 የፊዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት አውስትራሊያ ውስጥ ያለማቋረጥ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ያለው የኮሮናቫይረስ ተዛማችነት አበረታች መሆኑን ገለጡ።

ባለፉት 24 ሰዓታት እስከ ዛሬ ማክሰኞ ንጋት ድረስ በመላው አውስትራሊያ የተመዘገበው አዲስ በኮቪድ - 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ብቻ ነው።

አቶ ሃንት - አኃዞች እንዳመለከቱት ከሆነ የማኅበረሰብ ቫይረስ ተጋቦት ከማሽቆልቆሉም ባሻገር በመላ አገሪቱ የተመዘገበው አንድ ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል።

 

                   

ቫይረስ - ኒው ሳውዝ ዌይልስ

 

 የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት በዚህ ሳምንት መገባደጃ ላይ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎቻቸው ውስጥ ተማሪዎቻቸውን ፊት - ለፊት እንዲያስተምሩ ክፍት እንደሚሆኑና ሁለት አዋቂ ሰዎች ሌሎች ሰዎች ቤት ለመሄድ እንደሚችሉ አስታወቀ። 

ከዓርብ ሜይ 11 ጀምሮ መንግሥት ሕመም የተሰማቸው እስካልሆኑ ድረስ ሁለት አዋቂ ሰዎችና ልጆች ሌሎች ሰዎች ቤት ሄደው መጠያየቅ እንዲችሉ ፈቃዱ እንደሚሆን ገልጧል።  

ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ለውጦቹ እንዲካሄዱ መደረጉ የሚያመለክተው ኒው ሳውዝ ዌይልስ መልካም መሻሻልን እያሳየ መሆኑን ነው በማለት ስለምን መንግሥታቸው የጣላቸውን ገደቦች ለቀቅ በማድረግ ላይ እንዳለ ተናግረዋል።  

 

ቫይረስ - ቪክቶሪያ 

 

ቪክቶሪያ ሁለት አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችንና በቫይረሱ ሆስፒታል የገቡ ደርዘን ሰዎችን አስመዝግባለች።

ኒው ሳውዝ ዊውይልስ፣ ምዕራብ አውስትራሊያ፣ ኖርዘርን ቴሪቶሪና ኩዊንስላንድ የጣሏቸውን ገደቦች ለቀቅ ሲያደርጉ፤ ቪክቶሪያ ግና ያወጀችው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሜይ 11 እስከሚያበቃ ድረስ ለውጥ እንደማታደርግ አስታውቃለች። 

ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ መንግሥታቸው ስኬታማ የሆነ ስትራቴጂ ግብር ላይ ማዋሉንና ወረርሽኙም ገና ያላበቃ መሆኑን ገልጠዋል።

 

                                                     

                                

 

 

 

 

 

 

 

                                                      


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now