የሌበር ፓርቲ ምክር ቤት አባል ማይክ ኬሊ መሰናበት በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ወቅት የሟሟያ ምርጫን ግድ ሊል ነው

** በሰሜናዊ ግዛት የኮሮናቫይረስ ገደቦች ከነገ ጀምሮ ይላላሉ

Core bulletin 30 April 2020

Labor MP Mike Kelly. Source: AAP

ኬሊ ተሰነናበቱ

 

 የፌዴራል ሌበር ምክር ቤት አባል ማይክ ኬሊ በጤና ምክንያት ከፖለቲካው ዓለም በመሰናበታቸው ብርቱ ፉክክር የሚታይበት የማሟያ ምርጫ በደቡባዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ሊካሄድ ነው።

ኬሊ ለስንብታቸው ምክንያት የሆኑዋቸው ሕመሞች ኩላሊትና ሪህ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በምክር ቤት አባልነት የተመረጡበትን ኤደን ሞንኤይሮህን በሙሉ ብቃት እንዲያገለግሉ እንዳላስቹዋሏቸው ገልጠዋል። 

 የሌበር መሪ አንቶኒ አልባኒዚ የዶ/ር ኬሊን የ36 ዓመታት የሕዝብ ግልጋሎቶች አንስተው ምሥጋናና ሙገሳ አቅርበውላቸዋል፤ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውም ለፓርቲያቸውና ለወከሉት ሕዝብ ትልቅ እጦት እንደሆነም ጠቅሰዋል።  

ኬሊ በውትድርና ሕይወታቸው እስከ ኮሎኔል ማዕረግ ደርሰዋል። በግልጋሎታቸውም ወቅት ኢራቅ፣ ሶማሊያና ኢስት ቲሞር የውትድርና ግዳጃቸውን ለመወጣት ተሰማርተዋል።

ከ2007 ጀምሮ በዶ/ር ኬሊ ተይዞ የነበረውን የምክር ቤት ቤት ወንበር ለመተካት የሶስትዮሽ ፉክክር የሚደረግበት ሲሆን፤ ሌበር ወንበሩን የያዘው ከአንድ ፐርሰንት ባነሰ መጠን ነው። 

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ምክትል ፕሪሚየር ጆን ባሪላሮ ናሽናልስ ፓርቲን ወክለው እንደሚወዳደሩ ሲጠቆም፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ትራንስፖርት ሚኒስትር አንድሩ ኮንስታንስና ሴናተር ጂም ሞላን በሊብራል ፓርቲ በኩል ስማቸው በዕጩነት ተነስቷል።

ሌበር ዕጩውን ገና ይፋ አላደረገም።   

1600 Core bulletin 30 April 2020
Deputy Premier and Minister for Regional NSW John Barilaro speaks to the media during a press conference in Sydney. Source: AAP

ምንም እንኳ ማንኛው ናሽናልስ ፓርቲን ወክሎ በዕጩነት ሊቀርብ እነደሚገባ የሚወስነው ፓርቲው ቢሆንም የፓርቲው መሪና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማኮርማክ የአቶ ባሪላሮን ዕጩነት በመልካም ጎኑ እንደሚቀበሉ ከወዲሁ ገልጠዋል። 

 

                                                       

የቫይረስ ገደቦች መላላት

 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አውስትራሊያ ውስጥ ኮሮናቫይረስን በመክላት የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች።

በክፍለ ግዛቲቱ በኮቪድ - 19 ተጠቅተው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሶስት ብቻ ሲሆኑ፤ በቫይረሱ ተይዘው የነበሩ 103 የመዲናይቱ ካንብራ ነዋሪዎች ሁሉም አገግመው ተነስተዋል።

 

የጤና ሚኒስትር ራቼል ስቲፈን - ስሚዝ ምንም እንኳ ክፍለ ግዛቲቱ ቫይረሱን መክላት ቢቻላትም ቫይረሱ አውስትራሊያ ውስጥ ሰፍኖ ያለ መሆኑን ስለሚገነዘቡ የማኅበራዊ ርቀት ላይ ገደቦችን ለማላላት እንደማይጣደፉ አመላክተዋል። 

 

በአሁኑ ወቅት በመላው አውስትራሊያ 1,000 ያህል ሰዎች ገና ከቫይረሱ አላገገሙም። 

 

 

                                                       

 

 

የሰሜናዊ ግዛት መንግሥት በኮሮናቫይረስ ሰበብ ገደብ ተጥሎባቸው የነበሩ የንግድ ተቋማት በአብዛኛው በወርኃ ጁን ተከፍተው ሥራቸውን እንዲጀምሩ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

 

ከነገ ዓርብ ከቀትር በኋላ ጀምሮ አካላዊ ርቀት እንደተጠበቀ ሆኖ የመጫዎቻ ሥፍራዎች፣ የመዋኛ ቦታዎች፣ ስኬት ፓርኮች፣ አካላዊ እንቅስቃሴና የግል ልምምዶችን ማካሄድ ይቻላል።

ዋና ሚኒስትር ማይክል ገነር የገደቦችን መላላት አስመልክተው፤ አካላዊ ርቀቶች እስከተጠበቁ ድረስ ሠርጎች፣ ቀብሮችና በውጭ መሰባሰቦችን ማካሔድ መፈቀዱን ተግረዋል። 

 

አክለውም፤ ከሁለት ሰዓታት ባነሰ ጊዜያት የሚጠናቀቁ የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎች ከሜይ 15 ጀምሮ የሚፈቀዱ እንደሆነና ያም መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የአካል እንቅስቃሴ መሥሪያ ሥፍራዎች፣ ቤተ መጽሐፍትና የጥፍር ሳሎኖችን እንደሚያካትት ገልጠዋል። 

 

 

 

 

 


2 min read

Published

Updated


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now