በፌዴራል መንግሥቱ - የስቴትና ክፍለ ግዛት መንግሥታት በትምህርት ቤቶችን አከፋፈት ጉዳይ ላለመስማማት ተስማሙ

የሥራ አጥነት ቁጥር ጨመረ… ገና ያሻቅባል ተብሎ ተገምቷል

4pm Core bulletin 16 April 2020

Source: Courtesy of SBS/Omar Dabbagh

ቫይረስ - ትምህርት ቤቶች

 

 የጋራ ብልፅግናው - የስቴትና ክፍለ ግዛት መንግሥታት በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ሳቢያ በትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጉዳይ ላለመስማማት ተስማምተዋል።

በዛሬው ዕለት (ሐሙስ) የተካሄደው የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ የትምህርት አሰጣጥን አስመልክቶ ሰባት አገር አቀፍ መርሆዎችን አሳልፏል።

በስብሰባውም ወቅት ተማሪዎች ወረርሽኙ ሰፍኖ ባለበት ወቅት በአካል ተገኝተው ይማሩ አይማሩ የሚለው አጀንዳ ክርክር ተካሂዶበታል።

ምንም እንኳ አያሌ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከቤት ሆነው ቢከታተሉም ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነዋል። 

በብሔራዊ ካቢኔው መርሆዎች ውስጥ ቀውሱ ሰፍኖ ባለበት ወቅት ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዳይጓደልባቸው ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ተጠቅሷል። 

የመምህራንም ደህንነት በውል እንዲጠበቅ ተጠቅሷል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የተማሪዎቹና አስተማሪዎቹ የጤና ሁኔታ በተናጠል ምልከታ የተደረገበት መሆኑን ሲገልጡ፤

 "ልጆችን አስመልክቶ የጤና ምክሩ ግልጽ ነው፡፡ ለልጆች ደህንነት የተሻለው ሥፍራ ትምህርት ቤት ነው። ውዥንብሩ ያለው መምህራኑን አስመልክቶ ነው ብዬ አስባለሁ… አስተማሪዎች ከመማሪያ ክፍሎች ይልቅ በመምህራን ማረፊያ ክፍል ለጤና አደጋ የተጋለጡ ናቸው። እርግጥ ነው፤ በመሥሪያ ቤታቸው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። ተመሳሳይ ደንብ ተማሪዎችን አይመለከትም" ብለዋል።    

 

                                                 

 

ቫይረስ - ሥራ አጥነት

 

 የፌዴራል መንግሥቱ በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ሳቢያ ሥራ አጥነት ከአሁኑ በባሰ መልኩ ሊንር እንደሚችልና የመንግሥት ፖሊሲዎች የጉዳቱን መጠን ሊቀንሱት እንደሚችሉ ጠቁሟል። 

በወርኃ ማርች የሥራ አጥነት መጠን 5.2 ፐርሰንት በመድረሱ - በፌብሪዋሪ ከነበረው 5.1 የሥራ አጥነት መጠን በትንሹ ጨምሯል።

ይሁንና የሥራ አጥነት መጠኑ ዳታ የተሰበሰበው ኮሮናቫይረስ መጠነ ሰፊ ተፅዕኖ ከማሳደሩ በፊት ነው።

የሥራ ሚኒስትር ሚካኤላ ካሽ በመጪዎቹ ወራት ውስጥ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር ገልጠው፤ ሆኖም በመንግሥት የሥራ ጠባቂ ክፍያ አማካይነት በርካታ ሰዎች ሥራ አጥ ከመሆን እንደሚድኑ ተናግረዋል።  

"የሥራ አጥነቱ መጠን የኮቪድ - 19ኝን ተፅዕኖ እንደማያንጸባረቅ በማመኑ ረገድ የመጀመሪያው ነው። አዎን ሥራ አጥነት በጁን 10 ፐርሰንት ይደርሳል። ይህን አስመልክቶ የገንዘብ ሚኒስቴር በጣም - በጣም ግልጽ ነው። መንግሥት የሥራ ጠባቂ ክፍያን ባይዘረጋ ኖሮ መጠኑ 15 ፐርሰንት ደርሶ ትመለከቱ ነበር" ሲሉ አሳሳቢነቱን አመላክተዋል።

የሌበር ፓርቲ መንግሥት በሥራ ጠባቂ ክፍያ ፖሊሲው ውስጥ በፓርላማ የተሰጠውን መብት ተጠቅሞ ጊዜያዊ ሠራተኞችን እንዲያካትት ጥሪ አቅርቧል።

አሥር ፐርሰንት ሥራ አጥነት ማለት 1.4 ሚሊየን ሰዎች ሥራ አጥ ይሆናሉ ማለት ነው።

                                               

                                                 

 

የቫይረስ - ቁጥር 

 

 

በዓለም ላይ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 2 million ሲያልፍ አውስትራሊያ ውስጥ እያሽቆለቆለ ይገኛል።

 በአገር አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6458 ሲደርስ 63 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ ከፍተኛውን ቁጥር ይዘዋል።

 ኒው ሳውዝ ዌይልስ - በቫይረሱ የተያዙ 2897 ሕይወታቸውን ያጡ 25 ሲደርሱ፤

ቪክቶሪያ - 1299 በቫይረሱ ሲጠቁ 14 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል።

ኩዊንስላንድ 1001 በቫይረሱ ሲያዙ 5 ስዎች ለሕልፈተ ሕይወት በቅተዋል።

                                                      

 

ቫይረስ - ብስክሌት

 

 የ2020 ቱር ደ ፍራንስ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ለኦገስትና ሴፕቴምበር ተሸጋግሯል።

የብስክሌት ውድድሩ ሊካሄድ ተወጥኖ የነበረው ከ 27 ጁን እስከ 19 ጁላይ ባሉት ጊዜያት ነበር።

ውድድሩ ወደ ሌላ ወራት ሊሸጋሸግ የቻለው የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮንን እስከ ጁላይ አጋማሽ አንዳችም ሕዝባዊ ትዕይንቶች እንዳይካድ መወሰናቸውን ተከትሎ ነው።  

የውድድሩ ዳይሬክተር ክሪስቲያን ፕሩድሆም ከ29 ኦገስት እስከ 20 በሚካሄደው የሶስት ሳምንታት የብስክሌት ውድድር ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ የስፖርቱ አፍቃሪዎች በየዕለቱ በውድድሮቹ መስመሮች ላይ እንደሚገኙ ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል።

 

                                                      

 


3 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now