በአዲስ አበባ አሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች ሽግሽግና የሹመት አሰጣጥ ተካሄደ

*** የአንበጣ መንጋ ኢትዮጵያ ውስጥ 420 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት አድርሷል

Addis Ababa

Source: FBC

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትናንትናው ዕለት ለመዲናይቱ አሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች የኃላፊነት ሽግሽግና ሹመቶችን አደላድለዋል።

1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ

2ኛ. ዶክተር መስከረም ፈለቀ – ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

3ኛ . ኢንጂነር አያልነሽ ሀ/ማርያም – ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

4ኛ. ዶክተር መስከረም ምትኩ – የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

5ኛ. ዶክተር ሚልኬሳ  ጃጋማ – መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

6ኛ. ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ – ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

7ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ – ሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ

8ኛ. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ – ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን የአንበጣ ወረርሽኝ 420 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱንና ወረርሽኙን መቆጣጠር ከተቻለ እስከ 35 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጠዋል፡፤

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጡት ሰኞ ዕለት በአምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

የአንበጣ ወረርሽኙ በአፋር፣ ሶማሌ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ውስጥ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

የአንባጣውን ወረርሽኝን ለመግታት የኢትዮጵያ አየር መንግድንና የአገር መክላከያ ሠራዊትን ጨምሮ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መሆናቸውንና በቀጥታም የግብርና ሚኒስቴር በዋነኛነት የመከላከል ሂደቱን እየተገበረ እንዳለ አስታውቀዋል።


2 min read

Published


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now