SKIP TO MAIN CONTENT

"በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት በገንዘብ ሲተመን ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ይገመታል" ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

*** 1,338 ሄክታር (389,955 ካሬ) መሬት ተወርሯል፤ 21,695 የጋራ መኖርያ ቤቶች በሕገ ወጥ ሁኔታ ተይዘዋል፡፡

Adanech Abiebie
Adanech Abiebie, Deputy Mayor of the City of Addis Ababa Source: Adanech Abiebie/Twitter

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report


Skip to article content

 ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አስተዳደሩ ያስጠናውን የመሬት ወረራና ህገ ወጥ የኮንደሚኒየም ቤቶች ቅርምት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

 በዛሬው መግለጫቸው እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ፡

 ~ 1,338 ሄክታር (389,955 ካሬ) መሬት ተወርሯል፡፡

~ 322 ህንፃዎች ባለቤት የላቸውም፡፡

~ 21,695 የጋራ መኖርያ ቤቶች  በህገወጥ ሁኔታ ተይዘዋል፡፡

 ~ 14,641 መኖሪያና ለንግድ የተከራዩ የቀበሌ ቤቶችን ያለ አግባብና በህገ-ወጥ ይዞታነት ይገኛሉ፡፡

~ በህገ-ወጥ ወረራ የተያዘው መሬት በገንዘብ ሲተመን ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ይገመታል፡፡

~ በሪል ስቴት አልሚዎች፣ በግለሰቦች፣ በሀይማኖት ተቋማትና በቡድን በመደራጀትና መንደር በመመስረት ጭምር በሚገለፅ መልኩ የመሬት ወረራ ተፈፅሟል፡፡

~ 21,695 የጋራ መኖርያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው፡፡

~ 75% የኮንዶሚኒየሞች የተያዙት ባልተመዘገቡና ባልቆጠቡ ሰዎች ነው፡፡

 ~ 18,423 የኮንደሚንየም ቤቶች በህገወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው፡፡

~ 10,565 የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች  በህገወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው፡፡

~ 234 የቀበሌ ቤቶች የጠፉ ቤቶች ናቸው፡፡

~ 537 የቀበሌ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ወደ ግል ቤትነት የዞሩ ናቸው።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now