ስለ ኮቪድ-19 ክትባትና ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባቶች ሊያውቋቸው የሚገቡ

ከኦሚክሮን አስቸኳይነት ጋር ተያይዞ አውስትራሊያ ለኮቪድ-19 መስፋፋት ግብረ ምላሽ እየሰጠች ሳለ፤ ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት በብርቱ እየተካሄደ ነው። ሊያውቋቸው የሚገባዎት ምን እንደሆኑ እነሆ።

The Coordinator General of Operation COVID Shield Lieutenant General John Frewen receives his COVID-19 vaccination booster dose at Erindale Pharmacy in Canberra, Tuesday, December 14, 2021. (AAP Image/Lukas Coch) NO ARCHIVING

The Coordinator General of Operation COVID Shield Lieutenant General John Frewen receives his COVID-19 vaccination booster dose in Canberra. Source: AAPAAP Image/Lukas Coch

በመላው አውስትራሊያ ክፍለ አገራትና ግዛቶች ባለው ከፍተኛ የክትባት መጠን አስባብ የዓለም አቀፍ ጉዞ መቀጠልና የተጣሉ ገደቦች መነሳት ታይተዋል።

በሳቢያውም በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል፤ የኦሚክሮንና ዴልታ ቫይረሶች እጅግ ተዛማችነትን ተከትሎም የጤና ባለ ስልጣናት ሰዎች ብርቱ መከላከያ እንዲሆናቸው ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባቶችን እንዲከተቡ ጥሪዎችን እያቀረቡ ነው። 

የክትባት ቴክኖሎጂ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባቶች ምልከታ ከቀድሞዎቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባቶች ጋር ተመሳሳይ መሆንን አበክሮ ያመለክታል same as the first and second vaccine doses.

“ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት በተለይም በመላው ዓለም ሊስፋፋ ስለሚችለው ኦሚክሮን ቫይረስ ታካይ መከላከያነት በጣሙን አስፈላጊ ነው" ሲሉ የጤና ዲፓርትመንት ፀሐፊ ብሬንዳን መርፊ ወርኃ ዴሴምበር ውስጥ ተናግረዋል።

የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎች

የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ዴሴምበር መጀመሪያ ላይ የበዓል ሰሞን ከመጀመሩ በፊት አገር አቀፍ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻን አስጀምረዋል፤ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች የኦሚክሮን ቫይረስን ለመከላከል ካላቸው ውስን የመከላከል አቅም አስጊነት ጋር ተያይዞ አውስትራሊያውያን በተቻለ መጠን ፈጥነው እንዲከተቡም ማሳሳቢያ ተሰጥቶባቸዋል። 

በሳቢያውም የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ከዋነኛ ክትባት በኋላ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት መከተቢያ ተመካሪ ጊዜን ከስድስት ወራት ወደ አምስት ወራት ቀደም እንዲል አድርጓል recommended timing 

እስከ 1.5 ሚሊየን አውስትራሊያውያን አሁኑኑ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትን መከተብ ይችላሉ። 

የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ከፋይዘር በተጨማሪ የሞደርና ክትባትንም በተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትነት ግልጋሎት ላይ እንዲውል ይሁንታውን ቸሯል approved a Moderna vaccine 

ተሳትፎን ለማበረታታት የፌዴራልና ክፍለ አገራዊ መንግሥታት የተለያዩ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎችን በመላ አገሪቱ ያካሂዳሉ various booster campaigns

ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባቶች ለአረጋውያን

እንደ መንግሥት አማካሪ አባባል government advisory ዕድሜያቸው በ70ዎቹና ከዚያ በላይ ያለ አረጋውያን፣ ዕድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው፣ በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆነ፣ የአቦርጅናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሆነው ዕድሜያቸው 50 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ለኮሮናቫይረስ ከተጋለጡ ለብርቱ ሕመም ለመዳረግ ተጋላጭ ናቸው።

የፌዴራል ጤና ዲፓርትመንት ስታቲስቲክስ እንደሚያመለክተው statistics ከጃኑዋሪ 2020 ወዲህ 1,910 አረጋውያን አውስትራሊያውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
PM Morrison received his COVID-19 booster vaccination with elderly Jane Malysiak in NSW.
PM Scott Morrison received his COVID-19 booster vaccination alongside Jane Malysiak in NSW. Source: SMH POOL
በተለይም ለዴልታና ኦሚክሮን ተላላፊነት የተጋላጭነት መጠን ከፍተኛ ነው፤ ክትባት ለብርቱ ሕመም ወይም ለሞት ተጋላጭነትን በእጅጉ ዝቅ ያደርጋል።

በአገር አቀፉ ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት ቀዳሚ ተከታቢ የሆኑት አረጋውያን አውስትራሊያን ናቸው። 

ዕድሚያቸው 18 እና ከዚያም በላይ የሆነ አውስትራሊያውያን ለመደበኛውም ሆነ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትን ለመከተብ የመንግሥትን የክትባት መመዘኛ የሚያሟሉ ናቸው either booster vaccination 

በአረጋውያን የክብካቤ ተቋማት ያሉ አረጋውያን ቀዳሚውንም ሆነ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባቶችን በጋራ ብልፅግናው ክሊኒኮች ሊከተቡ ይችላሉ። 

የክብካቤ ተቋማቱ የክትባት ቀነ ቀጠሮን አስመልክቶ ከአረጋውያኑ ወይም የእነሱ ተለዋጭ ውሳኔ ሰጪዎች ጋር መወያየት ይችላሉ። 

ለአረጋውያን ክብካቤ ተቋም ነዋሪዎች ክትባትን አስመልክቶ ተጨማሪ ምክርን ካሹ ይህን ይጫኑ here ወይም ለተጨማሪ ክትባት ማጠናከሪያ ይህን ይጫኑ here

ክትባት ለልጆች

የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደርና የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከአምስት እስከ 11 ላሉ ልጆች ለፋይዘር ክትባት ጊዜያዊ ይሁንታን ሰጥተዋል provisionally approved the Pfizer vaccine 

ይሁንታው የተሰጠው በቅርብ የተካሄዱ ክሊኒካዊ የሙከራ ውጤቶች እንዳመለከቱት ክትባቱ ከፍተኛ ፍቱንነትን ያሳየና አብዛኛዎቹ የጎንዮሽ ጉዳቶች መለስተኛና ጊዜያዊ በመሆናቸው እንደሆነ የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Bookings for this vaccination ለዚህ ክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያስያዝ የሚቻል ሲሆን ክትባቱን መከተብ የሚጀምረው ግና ከጃኑዋሪ 10, 2022 ጀምሮ ነው።

ክትባቶቹን ከጠቅላላ ሐኪሞች፣ የአቦርጂናል ጤና አገልግሎቶች፣ የማኅበረሰብ መድኃኒት ቤቶችና የክፍለ አገርና ግዛት ክሊኒኮች ዘንድ መከተብ ይቻላል።
child vaccinated
Vaccinating children can help reduce community transmission and prevent them passing the virus onto the wider community. Source: Getty Images
የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን በሁለቱ ክትባቶች መካከል የስምንት ሳምንት ክፍተት እንዲኖር ምክረ ሃሳቡን የቸረ ሲሆን፤ ሆኖም እንደ ወረርሽኙ መዛመት ልዩ ሁኔታ ሲከሰት በመጀመሪያውና ሁለተኛው ክትባቶች መካከል ሊኖር የሚገባው ክፍተት ወደ ሶስት ሳምንት ዝቅ ሊል ይችላል። 

Children aged five to 11 years ዕድሜያቸው ከአምስት እስከ 11 ያሉና ለብርቱ ሕመሞች ተጋላጭ ሆነው ያሉ፣ የአቦርጅናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሕፃናትና በተፋፈገ ሁኔታዎች ውስጥ የሚኖሩ ወይም ወረርሽኑ በተዛመተበት አካባቢ ያሉ ከብርቱ ተጋላጭነትነታቸው አኳያ ከኮቪድ-19 ክትባት በጣሙን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን አመልክቷል።  

በእንዚህ ዕድሜ ክልል ያሉ ሆነው ቀደም ሲል በኮቪድ -19 ተጠቅተው የነበሩ ሕፃናት ከሕመማቸው ካገገሙ በኋላ መከተብ ይችላሉ። 

ለልጆች እንዲሰት ምክረ ሃሳብ የተቸረበት የክትባት መጠን ከአዋቂዎች ለየት ይላል፤ ዕድሜያቸው 12 እናን ከዚያ በላይ ላሉ የሚሰጠው የክትባት መጠን 30 ማይክሮግራምስ ሲሆን ለልጆች የሚሰተው 10 ማይክሮግራምስ ይሆናል። 

የመጀመሪያ ክትባታቸውን ከተከተቡ በኋላ ወደ 12 ዓመት ከፍ ያሉ ልጆች ቀጣዩን ሙሉ ክትባት የሚከተቡት አዋቂዎች የሚከተቡትን የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባት ይሆናል።

ተጨማሪ እርዳታን ማግኘት የምችለው ከየት ነው?

በዓለም የጤና ድርጅት ኦሚክሮን በ 'አሳስቢ ቫሪያንት' ከተፈረጀ በኋላ የፌዴራል መንግሥቱ ስለ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረቶቹን አድሷል።  

International students return to Australia
Booster doses provide an added layer of protection. Source: AAPAAP Image/Bianca De Marchi
የኮቪድ-19 ቀዳሚ ክብካቤ ግብረ ምላሽ አንደኛ ተቀዳሚ ረዳት ፀሐፊ ዶ/ር  ሉቃስ ዴ ቶካ explained  ታካይ የህክምና አማራጮች ቢኖሩ እንኳ further treatment options ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባቶች እንደምን ጠቃሚ እንደሆነ ሲያስረዱ፤

"አለመታደል ሆኖ፤ ኮቪድ-19ኝን አስመልክቶ የጎንዮሽ ጉዳት አልባ ሕክምና የለም" ብለዋል። 

ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባትን ከሁለተኛ ክትባት አምስተኛ ወራት በኋላ መከተብ ይቻላል፤ የሁለተኛ ክትባት ቀንም የተከታቢው ግለሰብ ዲጂታል የምስክር ወረቀት ላይ ሰፍሮ ይገኛል።  

ከዲሴምበር 15 ጀምሮ የልጆች ቀጠሮን አካትቶ ሁሉንም የክትባት ቀነ ቀጠሮዎችን በ vaccine clinic finder በኩል ማስያዝ ይቻላል። 

በሚኖሩበት ክፍለ አገር ተጥለው ያሉ ወቅታዊ ገደቦችን በ restriction checker አማካይነት መከታተል ይችላሉ።

ስለ ኮቪድ-19 መረጃን በቋንቋዎ በአስተርጓሚ በኩል ለማግኘት በ Australian Translating and Interpreting Services (ATIS) ድረገጽ በኩል ወይም 1800 131 450 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ስለ ኮቪድ-19 ክትባትና ቀነ ቀጠሮ ማስያዝን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፤ የብሔራዊ ኮሮናቫይረስ ቀጥታ መስመርን 1800 020 080 ይደውሉ።

ስለ ኮቪድ-19 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከሐኪምዎ ወይም የጤና ባለሙያ ጋር እንዲነጋገሩ ይመከራል።

እንደተመከረው ስለ ክትባቶች በቀጣይነት ሁሉንም ወቅታዊ መረጃ ለመረዳት SBS Coronavirus Portal በመጎብኘት በራስዎ ቋንቋ መረጃዎችን ያንብቡ። 


Share

Published

By Vrishali Jain
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service