አውስትራሊያ በኢትዮጵያ አዲስ አምባሳደር ሾመች

*** "ኢትዮጵያና አውስትራሊያ ቅልጡፍ የሆኑትን የአውስራሊያ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ፤ ጉልህ የሕዝብ-ለሕዝብ ትስስሮሻችንን መሠረት አድርጎ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚጋራ ነው" የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜሪዝ ፓይን

Julia Niblette, Australian Ambassador to Ethiopia.

Julia Niblette, Australian Ambassador to Ethiopia. Source: PMO

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜሪዝ ፓይን ወ/ሮ ጁሊያ ኒብሌት በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን አስታወቁ።

የአዲሷ አምባሳደር የሥራ ኃላፊነትም የአፍሪካ ኅብረትንና ተቀማጭ ያልሆኑባቸው አገራት የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጂቡቲንና ደቡብ ሱዳንንም እንደሚያካትት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ለSBS አማርኛ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።   

ሚኒስትር ፓይን አያይዘውም "ኢትዮጵያና አውስትራሊያ ቅልጡፍ የሆኑትን የአውስራሊያ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ፤ ጉልህ የሕዝብ-ለሕዝብ ትስስሮሽናችንን መሠረት አድርጎ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚጋራ ነው" ብለዋል። 

አውስትራሊያ በአውስትራሊያውያን የንግድ ማኅበረሰብ በኩል በታዳሽ ኃይል፣ ማዕድንና ግብርና መስክ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የሆነ የንግድ ፍላጎቶች አንዳሏትና የአውስትራሊያ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም በማኅበረሰብ ደረጃ ያሉ የግብረ አካል ጉዳተኞች፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃና የምግብ ዋስትና በመሳሰሉት ዘርፎች ጠቃሚ የሆኑ አስተዋፅዖዎችን እያበረከቱ እንደሚገኙ መግለጫው አመልክቷል።   

ሚንስትሯ አክለውም፤ አውስትራሊያ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ተከስቶ ያለው ሁኔታ አሳስቧት ያለ መሆኑንና፤ አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባትና በኅብረት የቆመች እንድትሆን ለሚደርጉት ጥረቶች ሁሉ ድጋፎቿን እንደምትቸርም አስታውቀዋል። 

 አውስትራሊያ ደቡብ ሱዳንን ከ2011 የነፃነት ጊዜ ጀምሮ እያገዘች እንደሆነና የአውስትራሊያ ወታደሮችም በተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም አስከባሪ ግዳጅ ውስጥ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውንም መግለጫው ጠቁሟል። 

በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ሆነው የተመደቡት ጁሊያ ኒብሌት በውጭ ጉዳዮችና ንግድ ዲፓርትመንት ውስጥ የኒው ሳውዝ ዌይልስ የውጭ ጉዳዮችና ንግድ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነው ሠርተዋል። ቀደም ሲልም በባንግላዴሽ የአውስትራሊያ አምባሳደር እንዲሁም በባንኮክ፣ ፓሪስና ማኒላ በዲፕሎማትነት አገልግለዋል።   

ወ/ሮ ኒብሌት ከሲዲኒ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ (Honours) እንዲሁም ከአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ሕግ የምሩቃን ዲፕሎማ አላቸው። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜሪዝ ፓይን ተሰናባች አምባሳደር ፒተር ዶይልና ቻርጄ ዲአፌይርስ ጄኒ ዳ ሪን ኢትዮጵያ ውስጥ ከ2018 አንስቶ እስከ 2021 የአውስትራሊያን ጥቅሞች በማስከበር ረገድ ስላበረከቱት አስተዋፅዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


2 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now