ባሕር ዳር ዳግም በሕወሓት ሮኬት መጠቃቷ ተነገረ

*** ሕወሓት በመንግሥት የአየር ጥቃት በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ አለ

Amhar Tigray Regions

Ethiopian military gathered on a road near the border of the Tigray and Amhara regions. Source: Ethiopian News Agency

የሕወሓት ቡድን እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ 7:40 ግድም የሮኪርት ጥቃት ማድረሱን አብመድ ዘግቧል።

በጥቃቱም በከተማይቱ ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለ በክልሉ ባለ ስልጣናት ተገልጧል።

ባለፈው ሳምንት በጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ላይ በሕወሓት የሮኬት ጥቃት ደርሶ በባሕር ዳር አውሮፕላን አካባቢ ጉዳት ደርሷል።

በወቅቱም የሕወሓት ቃል አቀባይ ድርጊቱን በሁለቱ ከተሞችና በኤርትራ መዲና አሥመራም በድርጅታቸው ተዋጊ ኃይላት መፈጸሙን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ሕወሓት በፌስቡክ ገጹ በመቀሌ መለስ ዜናዊ አካዳሚ ተማሪዎችና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የፌዴራል መንግሥቱ አየር ኃይል በሰነዘረው የአየር ጥቃት መቁሰላቸውን አስታውቋል።

የድርጅቱ መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልም መቀሌ ለአራተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት የደረሰባት መሆኑን ገልጸዋል።

በፌዴራል መንግሥቱ በኩል በርካታ ከተሞችን ከሕወሓት እጅ አላቅቆ ወደ መቀሌ እያመራ መሆኑ ተነግሯል። 

 


1 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now