በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋምና አካባቢውን መልሶ ለመገንባት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገለጠ

*** በሰሜን ሸዋ ሶስት ወረዳዎች ብቻ 281 ሰዎች መገደላቸውን፣ 246 ሺህ 818 ሰዎች እርዳታ ፈላጊ እንደሆኑ እና 9,661 ዜጎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ስለ መፈናቀላቸው በሪፖርት ተመለከተ።

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

በቅርቡ በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋም እና አካባቢውን መልሶ ለመገንባት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል መንግስት ገለፀ።

ይህ የተገለፀው አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም በክልል ደረጃ የተዋቀረው የቴክኒክ ኮሚቴ የምልከታ ሪፖርቱን ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረበበት ወቅት ነው።

በሰሜን ሸዋ ሶስት ወረዳዎች ብቻ 281 ሰዎች መገደላቸውን፣ 246 ሺህ 818 ሰዎች እርዳታ ፈላጊ እንደሆኑ እና 9,661 ዜጎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።

በ197 ዜጎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በጥቃቱ የመኖሪያ ቤቶች፣ የመንግስትና የግል ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ውድመት ደርሶባቸዋል፣ ዘረፋ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል።

በሸዋ ሮቢት፣ ቀወትና ኤፍራታ ግድም አራት ትምህርት ቤቶች እንደወደሙ እና ሰባት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ንብረታቸው እንደወደመ ተጠቅሷል።

ሶስት የጤና ተቋማት በጥቃቱ የወደሙ ሲሆን አንድ ጤና ተቋም ደግሞ ተዘርፏል ተብሏል።

ሰባት የእምነት ተቋማት መቃጠላቸው እና የውሃ መሰረተ ልማቶች ላይም ከባድ ጉዳት መደረሱ በሪፖርቱ ቀርቧል። የመንግስትና የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የተገለፀ ሲሆን አስራ አንድ ሆቴሎች እና አርባ ዘጠኝ የግል መጋዘኖች ተቃጥለዋል ተብሏል። እንስሳት መዘረፋቸውና የግብርና መሰረተ ልማቶች ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር፣ ሜዳ ላይ የወደቁ ዜጎችን በአስቸኳይ በማንሳት አካባቢውን መልሶ ለመገንባት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔርሰብ ዞን የደረሰውን ጉዳት የቴክኒክ ኮሚቴው እያጠናው እንዳለ እና በቅርቡ ሪፖርቱን እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

( ደመቀ ከበደ - አዲስ አበባ )


2 min read

Published

By Demeke Kebede


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now