SKIP TO MAIN CONTENT

የአማራ ክልል መንግስት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና አልሰጠሁም አለ

*** ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣ አካል ካለ የፀጥታ ኃይሉ እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል

Amhara Region
Gizachew Muluneh Source: FBC

1 min read

Published

Updated

By Stringer


Skip to article content

የአማራ ክልል መንግስት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አለመስጠቱን አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ጉዳዩን  አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የፊታችን ረቡዕ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱን አንስተዋል፡፡

በማህበራዊ  ሚዲያ የፊታችን ረቡዕ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የአማራ ክልል እንዲረጋጋ ለማይፈልጉ ሀይሎች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚመች መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ወቅቱ የተፈጥሮ አዳጋ የተከሰተበት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ አጀንዳ በሆነበት ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህጋዊ አይደለምም ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግስት ምንም አይነት ሰልፍ እንዳይካሄድ መወሰኑን ነው አቶ ግዛቸው የገለፁት፡፡

ይህን ተላልፎ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣ አካል ካለ ግን የፀጥታ ሀይሉ እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል፡፡

 

[ Fana ]


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now