የአማራ ክልል ምክር ቤት አዲስ የሥራ አስፈጻሚዎችን ሹመት አጸደቀ

*** አቶ ጌታቸው ጀበር ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነዋል

Homeland Report

Source: AMC

የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ መስራች ጉባኤው አዲስ የሥራ አስፈጻሚዎችን  ሹመት አጸደቀ።

ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እጩዎችን ለምክርቤቱ በማቅረብ ነው ሹመታቸው የጸደቀው.

በዚህም መሰረት:–

1ኛ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀበር (እጩ ዶክተር)

2ኛ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ሰማ ጥሩነህ (ዶክተር)

3ኛ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ

4ኛ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም ተሾመ

5ኛ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ

6ኛ የሥራና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ አቶ አረጋ ከበደ

7ኛ የፍትሕ ቢሮ ኀላፊ አቶ ገረመው ገብረ ጻዲቅ

8ኛ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ

9ኛ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

10ኛ የውኃና ኢነርጅ ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ማማሩ  አያሌው

11ኛ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ

12ኛ የማዕድን ቢሮ ኀላፊ አቶ ኀይሌ አበበ

13ኛ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ማተቤ ታፈረ

14ኛ የግብርና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ኀይለማርያም ክፊያለው

15ኛ የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ሜጀር ጀኔራል መሰለ በለጠ

16ኛ የንግድ ቢሮ ኀላፊ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ

17ኛ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኀላፊ ወይዘሮ ባንቸዓምላክ ገብረ ማርያም

18ኛ የመንገድ ቢሮ ኀላፊ አቶ መሃመድ ያሲን

19ኛ የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኀላፊ አቶ አማኑኤል ፈረደ

20ኛ የገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ፀጋ ጥበቡ

21ኛ የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ

22ኛ የቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ አቶ ጣሂር ሙሃመድ

23ኛ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኀላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ

24ኛ የፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ አንሙት በለጠ

25ኛ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ቢያዝን እንኳሆነ

26ኛ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ  ኀላፊ  አቶ እንድሪስ አብዱ

27ኛ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ኢንጂነር ዳኝነት ፈንታ ሆነው ተሹመዋል።

ርእስ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ሲደራጅ በአስመዘገቡት ውጤት አካቢቢና ማኀበራዊ ጉዳዮችን መሠረት በማድርግ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሹመቱም 75 በመቶ አዳዲስ ሥራ አስፈጻሚዎች 25 በመቶ ደግሞ ነባር ናቸው ብለዋል።

[ አሚኮ ]

 

 


2 min read

Published

By Stringer Report


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now