እየተካሄደ ባለው አዲሱ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ ጉባኤ የብልጽግና ፓርቲ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ የነበሩትን ዶክተር ይልቃል ከፋለን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ መስራች ጉባኤው ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋየን የክልል ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል፡፡
የቀድሞው የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቀሰሙ ማሞ አዲስ ለተመረጡት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል፡፡
አቶ አማረ ሰጤ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነዋል።
የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ለዶር ይልቃል ከፋለ የስልጣን ርክክብ ፈፅመዋል።
አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
- የህልውና ዘመቻው በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ህዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲያገኝ፣
- የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲቋቋሙና ድጋፍ እንዲደረግላቸው፣
- የክልሉ አስር ዓመት መሪ እቅድ ለማሳካት [ በግብርና፣ የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም መሰረተ ልማት ግንባታ] እቅዶችን
- የአገልግሎት አሰጣጥ፤ መልካም አስተዳደርና ሚዛናዊ የንግድ ስርዓት ለማስፈን፣
- በክልሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የአስተዳደር እና አስፈጻሚ አካል እንዲቋቋም
ልዩ ትኩረት አደርጋለሁ ብለዋል።

