በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሓት መካከል ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት በተካሔደው የሰላም ንግግር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በስምምነት ሰነዱ ላይ ከሠፈሩት አንኳር ነጥቦች ውስጥ፤
- በሁለቱ ወገኖች ዘንድ የተኩስ ልውውጥ መገታት
- ትግራይ ክልል ውስጥ በግጭቱ ሳቢያ የተናጋውን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መልሶ ማበጀት
- ከአመፅ እርምጃ ተገትቶ ልዩነቶችን በፖለቲካዊ መንገድ መፍታት
- የደኅንነት ሁኔታ ለሁሉም ማስገኘት
- ዘላቂ ስምምነት ላይ መድረስ
- ለግጭት ሳቢያ ሆነው ለተነሱ ችግሮች ማዕቀፋዊ ዕልባት ማበጀት
- የትጥቅ ፍቺ መካሔድ
- ዕርቅ ማውረድና ማኅበራዊ ትስስሮሽን መልሶ ማበጀት
- ኢትዮጵያ አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ያላት የመሆኑ አመኔታ
- ስምምነቱ በተካሔደ 24 ሰዓታት ውስጥ የሁለቱ ተስማሚ ወገን ወታደራዊ አመራሮች ለስምምነቱ ትግበራ ንግግር ማካሔድ
- የጠብ ጫሪ ፕሮፖጋንዳ ድምፆችን ከማስተጋባት መቆጠብ
- ሰብዓዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ
- ዝርዝር ፖለቲካዊ ዕልባት ላይ መድረስና ግብር ላይ ማዋል
የሚሉ ይገኙበታል።
ዝርዝር ሒደቶችን አስመልክቶ በተከታታይ የጋራና የተናጠል መግለጫዎች በሁለቱ ወገኖች በኩል የሚሰጡ ይሆናል።
የስምምነቱን ፊርማ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተሳታፊዎችና ሸምጋዮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

