SKIP TO MAIN CONTENT

የባሕር ማዶ ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ የኮሮናቫይረስ ነጻ ማረጋገጫ በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ

ቀደም ሲል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የኮሮናቫይረስ ነጻ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ይጠየቁ የነበረው በ72 ሰዓታ ውስጥ ነበር።

Amharic Homeland  News July 17, 2020
Dr Liya Tadesse, Minister for Health Source: Courtesy of ENA

1 min read

Published

By Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የቫይረስ ነጻ ማረጋገጫ መመሪያው ከ72 ሰዓታት ወደ አምስት ቀናት እንዲለወጥ የተደረገው በርካታ መንገደኞች ከመነሻቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ ከ72 ሰዓታት በላይ እንደሚፈጅባቸው በመጥቀስ የማሻሻያ ጥያቄዎችን ማቅረብ ከግምት ውስጥ ገብቶ መሆኑን የጤና ሚንስትር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል። 

ድንጋጌው ላይ ማሻሻያ ያደረገው የሚኒስትሮች ኮቪድ - 19 ኮሚቴ ነው።

በማሻሻያ ድንጋጌው ላይ የቴክኒክ ቡድኑም መክሮ ይሁንታውን የቸረ መሆኑ ተገልጧል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም በአምስት ቀናት ውስጥ የኮሮናቫይረስ ነጻ ማረጋገጫ ያላቸው መንገደኞች አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ናሙና ሰጥተው ወደ አገር ከዘለቁ በኋላ ቀደም ሲል እንደነበረው ለ 14 ቀናት ወሸባ አይገቡም።

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now