የአዲሱ ሌበር መንግሥት ሚኒስትሮች ቃለ መሃላ ፈፀሙ

*** ራፋዔል ናዳል ኖቫክ ጆኮቪችን በፈረንሳይ ኦፕን የሩብ ማጣሪያ ውድድር ረታ።

SBS News in Macedonain 1 June 2022

Prime Minister Anthony Albanese poses with his new Ministry after a swearing-in ceremony at Government House on June 01, 2022 in Canberra, Australia. Source: Getty Images

የሌበር አዲሱ መንግሥት ሚኒስትሮች ዛሬ ከቀትር በፊት ቃለ መሃላ ፈፀሙ።

ቃለ መሃላ ከፈፀሙት 30 ሚኒስትሮች ውስጥ 13ቱ ሴት ሚኒስትሮች ናቸው።

News
Prime Minister Anthony Albanese poses for a group photo with his female ministers after a swearing-in ceremony at Government House on June 01, 2022 in Canberra, Source: Getty

የሴት ሚኒስትሮች ቁጥር ብዛት በአውስትራሊያ መንግሥት ታሪክ የመጀመሪያው ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ከአዲሱ ሚኒስትሮቻቸው ውስጥ ሁለት ሙስሊም ሚኒስትሮችን ኢድ ሁሲክና አን አሊን አካትተዋል።

News
Australian Industry and Innovation Minister Ed Husic (L), and Australian Minister for Early Childhood shakes hands with Australian Governor-General David Hurley Source: AAP

ሊንዳ በርኒ የመጀመሪያዋ ሴት የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል። 

News
Linda Burney Australian Minister for Indigenous Australians is congratulated by Australian Governor-General David Hurley at Government House on June 01, 2022. Source: Getty

ምጣኔ ሃብት

የአውስትራሊያ ምጣኔ ሃብት በማርች ሩብ ዓመት በ 0.8 ፐርሰንት አድጓል። 

የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ እንደገለጠው ለማርች ሩብ ዓመት ምጣኔ ሃብት ዕድገት ማሳየት የኮቪድ-19 ገደቦች መነሳትን ተከትሎ ግለሰቦችና መንግሥት ገንዘቦቻቸውን ማውጣት መጀመራቸው አጋዥ ሆኗል። 

ይሁንና በሌላ በኩል የምጣኔ ሃብት ተጠባቢዎች በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ በሚሰበሰብበት ወቅት የወለድ መጠን እንዳይጨምር የሚከላከል አይሆንም የሚል አተያይ እየሰነዘሩ ነው።  

ቴኒስ

ራፋኤል ናዳል ለፈረንሳይ ኦፕን የሩብ ማጣሪያ ውድድር ኖቫክ ጆኮቪችን 6-2, 4-6, 6-2, 7-6 (7-4) በሆነ ውጤት ረትቷል።

በውጤቱም ናዳል ለ14ኛ ጊዜ የሸክላ ሜዳ ቴኒስ አሸናፊነት ተቃርቧል።

News
Winner Rafael Nadal of Spain is congratulated at the net by Novak Djokovic of Serbia on Court Philippe Chatrier after the singles Quarter Final match at the2022 Source: Getty

ናዳል በጠቅላላው የ22 ዋነኛ የቴኒስ ውድድር ሻምፒዮን ነው። 

ጆኮቪች እስካሁን 20 ዋነኛ የቴኒስ ውድድር ሻምፒዮና አሸናፊ በመሆን ይከተላል። 

 

 

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now