የአውስትራሊያ ማዕከላዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ዛሬ ማክሰኞ ኦገስት 2 / ሐምሌ 26 የ1.85 ፐርሰንት ጭማሪ አድርጓል።
የዛሬው ጭማሪ የተደረገው ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ ነው።
የባንኩ ገዢ ፊሊፕ ሎዊ እርምጃው የአውስትራሊያን ፋይናንስ ሁኔታ ለማርጋት የተወሰደ ተጨማሪ እርምጃ እንደሆነ ገልጠዋል።
እንደ ሬትሲቲ ስሌት ለ25 ዓመታት የ $500,000 የቤት ብድር ያለባቸው ግለሰቦች በአራቱ ተከታታይ ተጨማሪ የወለድ መጠኖች ሳቢያ በወር $472 ተጨማሪ ክፍያ ለማድረግ ግድ ይሰኛሉ።
የፌዴራል በጅሮንድ ጂም ቻልመርስ ዛሬ ፓርላማ ውስጥ ይህንኑ ጭማሪ አስመልክተው ሲናገሩ፤
"የቤት ብድራቸውን ለመክፈል ለሚጥሩ አውስትራሊያውያን አዋኪ ቀን ነው"
"ውሳኔው ለማንም ድንገተኛ አይደለም፣ አስደንጋጭም አይደለም። እንዲያም ሆኖ ግና ተናዳፊ ነው"ብለዋል።
አክለውም፤ ቤተሰቦች ዋጋቸው አሻቅበው ባሉት የግሮሰሪ፣ የነዳጅና ሌሎች ወጪዎች ጋር ለማቻቻል ጫና የበዛበት ውሳኔዎች ላይ ለመድረስ ግድ እንደሚሰኙ አመላክተዋል።