ጠ/ሚ ስኮት ሞሪሰን በቀጥታ ለቻይና ዜጎች መልዕክት አስተላለፉ

*** ቪክቶሪያ ከማኅበረሰብ ኮሮናቫይረስ ተጋቦት ነፃ የሆኑ 33 ቀናትን በተከታታይ አስቆጠረች

Zhao Lijian

Source: AAP

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በቻይናውያን ዘንድ ዝነኛ በሆነው የማኅበራዊ ሚዲያ ዊቻት በሚሊየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን የአውስትራሊያን አተያይ የሚያንንጸባርቅ መልዕክት አስተላልፈዋል። 

የመልዕክታቸው ትኩረትም በቅርቡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛኦ ሊያን በቲዊተር ገጻቸው አንድ የአውስትራሊያ ወታደር በአፍጋኒስታን ሕጻን ልጅ አንገት ላይ ስለት ይዞ የሚያሳየውን የአንድ ቻይናዊ ሰዓሊ ቅብ ስርጭት የሚመለከት ነው።

አቶ ሞሪሰን በመልዕክታቸው "ለአውስትራሊያ የአውስትራሊያን መደበኛ ልብስ ለለበሱ ሁሉ ጥልቅ የሆነ ክብር አለኝ። በብርቱ የግልጋሎት ሥራቸውና ለአውስትራሊያውን ደህንነትንና ለአውስትራሊያ ላበረከቱት አይታክቴ የጥበቃ ተግባራትም እኮራለሁ።

ለአገራችንና ለዕሴቶቿም ባላቸው ታማኝነት እኮራለሁ" ብለዋል።  

አያይዘውም አውስትራሊያ "ነፃና ዲሞክራሲያዊት አገር" ሆና እንደምትቀጥልና "ለዕውነተኛ ዕሴቶቻችን ታማኝና ሉዓላዊነታችንንም አስከባሪዎች ሆነን እንዘልቃለን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።

የቻይናውያን - አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ አባላትንም ከጎናቸው ሲያሰልፉ ክስተቱ "አውስትራሊያ ውስጥ ላለው የቻይናውያን ማኅበረሰብ ያለንን ከበሬታ ወይም ከቻይና ሕዝብ ጋር ያለንን ወዳጅነት አያጠፋም" 

"ተከታታይ መጤ ቻይናውያን ለአውስትራሊያ ላበረከቱት አስተዋፅዖዎች ከፍተኛ ዋጋና ጥልቅ አድናቆት አለን"

"ከ200 ዓመታት በላይ ቻይናዊ ዝሪያ ያላቸው አውስትራሊያውያን ብርቱ የሆኑ አስተዋፅዖዎችን ለአገራችን አበርክተዋል" ብለዋል። 

በሌላ በኩል ግና በቻይናና አውስትራሊያ ዘንድ ሰሞነኛ ለሆነው ውዝግብ ምንጭ የሆነውና ምስሉን የፈጠረው ቻይናዊው ሰዓሊ ፉ ዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንን ይቅርታ አልጠይቅም ሲል ምላሽ ሰጥቷል። 

አቶ ሞሪሰን ከጥቂት ቀናት በፊት ምስሉን አስመልክቶ ቻይና ይቅርታ እንድትል ጠይቀው ነበር።

---------------------------

ቪክቶሪያ ለ33 ተከታታይ ቀናት ከማኅበረሰብ ተጋቦት ኮሮናቫይረስ ነፃ ሆና ቆይታለች። 

ኒው ሳውዝ ዌይልስም በበኩሏ 25 ተከታታይ ቀናት ከማኅበረሰብ ተጋቦት ኮሮናቫይረስ ነፃ ሆና ቆይታለች። 

 

 

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now