የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14 ቀን 2013 በሚካሔደው አገር አቀፍ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ድምፅ የማይሰጥባቸውን አካባቢዎች አስታወቀ።
በቦርዱ ማብራሪያ መሠረት፤
1. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከዚህ በፊት የተጠቀሱት አራቱም (መተከል፣ ሺናሻ ልዩ፣ ካማሽ እና ዳለቲ) የምርጫ ክልሎች ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ የመስጠት ተግባር አይከናወንባቸውም፣ ቦርዱ ተጨማሪ የአፈጻጸም ሁኔታዎችን ለወደፊት የሚያሳውቅ ይሆናል።
2. በሶማሌ ክልል 14 ምርጫ ክልሎች ላይ (11ዱ ምርጫ ክልሎች ምርመራ ላይ ያሉ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ድምጽ የመስጠት ሂደት ለማካሄድ አስቸጋሪ ይሆናሉ የተባሉ ሲሆን ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ላይ የታየ መጠነ ሰፊ የአሰራር ችግር አለ በሚል የቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ የአጣሪ ቡድን አሰማርቶ የማጣራት ተግባሩን አጠናቋል፣ በዚህም መሰረት የአጣሪ ቡድኑን ግኝት መሰረት አድርጎ ድምጽ መስጠት ሊከናወንባቸው የሚችል ምርጫ ክልሎች ካሉ ለይቶ የሚያሳውቅ ይሆናል።
3. በኦሮሚያ ክልል ከዚህ በፊት እንደተጠቀሰው ሰባት ምርጫ ክልሎች (ቤጊ፣ ሰኞ ገበያ፣ አያና፣ገሊላ፣አሊቦ፣ጊዳሚ፣ ኮምቦልቻ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ የመስጠት ተግባር አይከናወንባቸውም።
4. አማራ ክልል ከዚህ በፊት ከተጠቀሱት ስምንት ምርጫ ክልሎች መካከል ድልይብዛ ምርጫ ክልል ላይ ቦርዱ ሰኔ 14 ቀን 2013 ድምጽ መስጠት ሂደት አንዲከናወን ወስኗል። ይህም ከክልሉ መንግስት በተሰጠ ማረጋገጫ መሰረት የመራጮች ምዝገባ በተስተጓጎለባቸው አምስት ምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ ያሉ ዜጎች ሌሎች ጣቢያዎች ላይ መመዝገባቸው በመረጋገጡ ነው።
በሌላ በኩል ግን በአማራ ክልል አንኮበር የምርጫ ክልል ድምጽ መስጠት ሰኔ 14 ቀን እንደማይካሄድም ቦርዱ ወስኗል፣ ቦርዱ ይህንን የወሰነው የአርጎባ ልዩ ምርጫ ክልል ላይ ድምጽ የሚሰጡ ዜጎች ለክልል ምክር ቤት በዚህ ምርጫ ክልል ድምጽ የሚሰጡ በመሆኑ እና በአካባቢው ባለ የጸጥታ ችግር ምክንያት ባለመመዝገባቸው ነው። በዚህም መሰረት በአማራ ክልል በስምንት ምርጫ ክልሎች ሰኔ 14 ቀን ድምጽ መስጠት ሂደቱ አይከናወንም።
5. በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ከዚህ በፊት ከተጠቀሱት አራት የምርጫ ክልሎች በተጨማሪ ማጀት መደበኛ የምርጫ ክልል ሰኔ 14 ቀን ድምጽ አይሰጥበትም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በሱርማ፤ በዲዚ፣ በሜኢኔት ልዩ የሚኖሩ ከብሔሩ ውጪ ያሉ ዜጐች ለተወካዮች ም/ቤት በማጀት መደበኛ ላይ ድምፅ ስለሚሰጡ እና የተጠቀሱት ቦታዎች ምዝገባ ስላልተከናወነ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ጉራፈርዳ ላይ ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ የጸጥታ ችግር ሸኮ ልዩ የምርጫ ክልል እና ቴፒ ምርጫ ክልል ሰኔ 14 ቀን ድምጽ መስጠት አይከናወንም። በዚህም ምክንያት ደ/ብ/ብ/ህ ክልል ሰባት ምርጫ ክልሎች ላይ በእለቱ ድምጽ አይሰጥም።
ቦርዱ በየጊዜው የሚያደርጋቸውን የሁኔታ ግምገማዎች የሚያሳውቅ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ቫይረስ ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ ያለው የአንድ ሳምንት የኮሮናቫይረስ ገደብ ነገ ሐሙስ ሊያበቃ ተቃርቦ ባለበት ወቅት በዛሬው ዕለት ረቡዕ ሜይ 2 ከ51,000 ምርመራዎች ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ስድስት ስዎች ተገኝተዋል። በጠቅላላው 67 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
በመላው ቪክቶሪያ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ 320 አካባቢዎች ተመዝግበዋል። በቫይረሱ ከተጠቁ ሰዎች ጋር የቅርብ ንኪኪ ነበራቸው ከተባሉት 4,800 ሰዎች ውስጥ 75 ፐርሰንቱ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ታውቋል።
የቫይረሱ የማኅበረሰብ ተጋቦት አለመቀነስን ተከትሎም ምናልባትም ተጥሎ ያለው ገደብ ሊራዘም ይችል ይሆናል የሚል ስጋትን አሳድሯል።

