Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

የአውስትራሊያ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ በ5.75 ፐርሰንት ከፍ አለ

ከጁላይ 1 አንስቶ የአውስትራሊያ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች በሰዓት $22.60 ይታሰብላቸዋል፤ ጭማሪያቸውም በሳምንት 47 ዶላር ይሆናል።

The pay increase will come into effect from 1 July.jpg

Credit: AAP / Bianca De Marchi

2.7 ሚሊየን ዝቅተኛ ተከፋይ አውስትራሊያውያን ከጁላይ አንድ አንስቶ በሳምንት የ47 ዶላር የደመወዝ ጭማሪ ማግኘት ይጀምራሉ።

 ለ5.75 ፐርሰንት የደመወዝ ጭማሪው ይሁንታውን የቸረው የፍትሕ ሥራ ኮሚሽን ካካሔደው ብሔራዊ የደመወዝ ክለሳ ተነስቶ መሆኑን አስታውቋል።

የፌዴራል መንግሥቱ የጭማሪ መጠን ሳይጠቅስ እያሻቀበ ካለው የዋጋ ግሽበት አኳያ ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ድጋፉን የቸረ ሲሆን፤ የአውስትራሊያ ሠራተኞች ምክር ቤት የ7 ፐርሰንት ጭማሪ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

ጭማሪው ከ4 ፐርሰንት እንዳያልፍ አሳስቦ የነበረው የአውስትራሊያ የንግድ ምክር ቤትና ኢንዱስትሪ የ 5.75 ፐርሰንት የደመወዝ ዕድገት አነስተኛ ንግዶችን ሊጎዳ ይችላል ሲል ቅሬታውን ገልጧል።


1 min read

Published

By NACA, Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now