ኢሰመኮ የመንግሥት የፀጥታ አካላት አላስፈላጊና ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል የመጠቀም አዝማሚያ እየጨመረ መምጣቱንና በሳቢያውም የሞትና አካል ጉዳት እየደረሰ መሆኑን አመለከተ

"ለሰው ሕይወት እልፈትና አካል ጉዳት ተጠያቂ የሆኑ የጸጥታ አካላት ተለይተው በሕግ እንዲጠየቁ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ወንጀል ስለመፈጸማቸው በቂ ጥርጣሬ ከሌለ እና ተዓማኒ ክስ የማይቀርብ ከሆነ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ወይም በሕግ አግባብ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች የዋስትና መብት ሊከበር ይገባል" የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

Al-Noor mosque.jpg

Al-Noor mosque Addis Ababa, Ethiopia. Credit: Giorgio Cosulich/Getty Images

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትናንት ግንቦት 24 ቀን 2015 "በሸገር ከተማ ከመስጊዶች መፍረስ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችንና የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ" በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ከግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለይም በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ውስጥ እና በተወሰኑ አካባቢዎች በሸገር ከተማ በመንግሥት አካላት ከፈረሱ መስጊዶች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን አስመልክቶ ማስረጃ በማሰባሰብና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የደረሱትን ሕልፈተ ሕይወቶችና ጉዳቶችን በተመለከተም ማስረጃዎቹን እያሰባሰበና ክትትል እያደረገ ያለውም፤ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ኃላፊዎች፣ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች፣ የዐይን እማኞችና ከተጎጂዎች መሆኑን አመልክቷል።

ኮሚሽኑ እስከ ትናንት ግንቦት 24 ድረስ ባሰባሰበው መረጃና ማስረጃዎች መሠረት የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችና የአድማ ብተና ኃይል ወደ ታላቁ አንዋር መስጊድ ግቢ ጭምር በመግባትና አስለቃሽ ጋዝ በመተኮስ ምእመናንን እና የተሰበሰበውን ሰው ለመበተን እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት የ2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ በርካቶች ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን፣ በጸጥታ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት መድረሱን እና በወቅቱ ወደ 140 የሚሆኑ ሰዎች በጥፋት ተጠርጥረዋል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑን ገልጧል።

ኢሰመኮ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በማንኛውም ዓይነት ሰላማዊ ሕዝባዊ ሰልፎች፣ ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ስብስቦችን አላስፈላጊና ተመጣጣኝ ካልሆነ እና ሞት ከሚያስከትል የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠቡ ዳግም ማሳሳቢያ አቅርቧል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል ጉዳዩን አስመልክተው "ለሰው ሕይወት እልፈትና አካል ጉዳት ተጠያቂ የሆኑ የጸጥታ አካላት ተለይተው በሕግ እንዲጠየቁ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ወንጀል ስለመፈጸማቸው በቂ ጥርጣሬ ከሌለ እና ተዓማኒ ክስ የማይቀርብ ከሆነ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ወይም በሕግ አግባብ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች የዋስትና መብት ሊከበር ይገባል" ብለዋል።



Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service