በጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረገ የአራተኛ ሰው አስከሬን ሊዝሞር - ኒው ሳውዝ ዌይልስ ተገኘ።
የኒው ሳዝ ዌይልስ ፖሊስ ደሜ ሊዝሞር ጎርፍ ባጥለቀቅልቀው አንድ መኖሪያ ቤት ዕድያቸው 70 ዓመት የደረሰ ግለሰብ ሞተው መገኘታቸውን አስታውቋል።
ይሁንና የግለሰቡ ማንነት ገና አልተለየም።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ምክትል ፕሪሚየር ፓል ቱሊ ከስተቱ እጅጉን አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል። ተጨማሪ ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረጉ ሰዎች ሊኖሩም እንደሚችሉ አመላክተዋል።
ቀደም ሲልም አንድ የ54 ዓመት ሰው አስከሬን መኪና ውስጥ የተገኘ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም የሁለት አረጋውያን ሴቶች አስከሬን መኖሪያ ቤቶቻቸው ውስጥ ተገኝቷል።
ዩክሬይን ዩናይትድ ስቴትስ
ዩናይትድ ስቴትስ የሩስያ አውሮፕላኖች በአየር ክልሏ እንዳያልፉ አገደች።
እገዳውን ያስታወቁት በዛሬው ዕለት ማክሰኞ ማርች 2 ለሁለቱ የጣምራ ምክር ቤት አባላት የመጀመሪያ ዓመታዊ ንግግራቸውን ያሰሙት ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ናቸው።
በዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬይን አምባሳደር ኦክሳና ማርካሮቫ በፕሬዚደንቱ ተጋባዥ እንግዳነት ከቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ጎን ተቀምጠው ታድመዋል።
ፕሬዚደንት ባይደን ወደ አምባሳደሯ በማመላከት የሩስያን ወረራ ተከትሎ ዩክሬይናውያን ያሳዩትን ጥንካሬ አንስተው በተናገሩበት ወቅት የምክር ቤት አባላቱ ከመቀመጫቸው ተነስተው አጋርነታቸውንና ከበሬታቸውን ገልጠውላቸዋል።

