ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በጎርፍ አደጋ ሳቢያ የሁለተኛ ሰው ሕይወት አለፈ

*** ሩስያ የኪየቭ ነዋሪዎች ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀች

News

Flooding occurs in the town of Lismore, northeastern New South Wales, Monday, 28 February, 2022. Source: AAP

በጎርፍ አደጋ ሳቢያ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ የሁለተኛ ሰው ሕይወት ተቀጠፈ። 

ትናንት ማክሰኞ ማርች 1 አንዲት የ80 ዓመት አረጋዊት ሊዝሞር ካለ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሕይወታቸው አልፎ ተገኝተዋል። 

የጎርፍ መጥለቅለቅ ደርሶባቸው የነበሩ የተወሰኑ የሊዝሞር አካባቢ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው ተመልሰው የማፅዳት ተግባር መጀመራቸውን ለ ABC የዜና አገልግሎት ገልጠዋል።

በሌላ በኩል ግና የዋራጋምባ ግድብ ሞልቶ መፍሰስ መጀመሩንና ይህም ለሁለት ሳምንታት ያህል ሊቀጥል ስለሚችል በሺህዎች የሚቆጠሩ የሆውከስባርይ እና ኒፒያን አካባቢ ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን እንደሚያሰጋ የኒው ሳውዝ ዌይልስ መንግሥት አስታውቋል። 

ጎርፍ ኩዊንስላንድ 

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ለደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ ሎጋን አካባቢ የተሰጠው የከባድ ጎርፍ ማስጠንቀቂያ ፀንቶ እንዳለ ነው። የጎርፍ መጠኑ 10.7 ሜትር በመድረስ የዛሬ አምስት ዓመትታ በፊት ከተከሰተው ከፍ ያለ ሬኮርድ አስመዝግቧል።     

በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ቤቶቻቸው በጎርፍ በመጥለቅለቃቸውና ከሌሎች ቀዬዎችም በመነጠላቸው ትናንት ማምሻውን አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ እገዛ ተደርጎላቸዋል። 

የሜትሮሎጂ ቢሮ ከዛሬ ማርች 2 ቀትር በኋላ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ብርቱ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል። 

የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓላሼይ ተከታታይ ሁነቶቹ ከፍተኛ የፋይናንስ ወጪንም እንደሚያስከትል ለቻናል ዘጠኝ ተናግረዋል።                          

ሩስያ ዩክሬይን 

ክሬምሊን የሩስያ ጦር የዩክሬይን ከተሞች ላይ የሚሰነዝረውን ማጥቃት አስመልክቶ የኪየቭ ነዋሪዎች ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀ። 

የ64 ኪሎ ሜትሮች ርዝመት ያለው የሩስያ ታንኮችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ቅልፈት ወደ መዲናይቱ እያመራ ሲሆን፤ የዩክሬይን የፀጥታ አገልግሎትና የኮሙዩኒኬሽን ጣቢያዎች ላይ ብርቱ ጥቃቶችን እንደሚሰነዝር ይጠበቃል።    

የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቫሎድሚር ዜሌንስኪ የተኩስ አቁም ንግግር ከመቀጠሉ በፊት ሩስያ የዩክሬይን ከተሞች ላይ የቦምብ ጥቃቶችን ከመሰንዘር የግድ መገታት እንዳለባት አሳስበዋል።

 ቫይረስ ሞሪሰን

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ትናንት ማርች 1 ማምሻው ላይ በኮቪድ-19 መያዛቸውን አስታወቁ። 

አቶ ሞሪሰን ሲድኒ በሚገኝው ቤታቸው ወሸባ መግባታቸውንና እዚያም ሆነው የጤና መመሪያዎችን ተከትለው ሥራቸውን እንደሚሠሩ ገልጠዋል።  

የአቶ ሞሪሰን ባለቤትና ልጆቻቸው በቫይረሱ ያልተያዙ ሲሆን፤ የቅርብ ንኪኪ ያላቸው በመሆኑ ለሰባት ቀናት ወሸባ ገብተው ይቆያሉ። 


2 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now