የአልባኒዚ መንግሥት ትናንት ተጀምሮ ዛሬ በሚያበቃው የሁለት ቀናት አገር አቀፍ የሥራዎችና ክህሎቶች ጉባኤ በዘንድሮው የፋይናንስ ዓመት 195 ሺህ ባለ ክህሎት ሠራተኞችን ወደ አውስትራሊያ እንዲገቡ የሚያደርግ መሆኑን አስታወቀ።
ይህንን የሠራተኞች ጣራ ገደብ ይፋ ያደረጉት የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ክሌየር ኦኒል ናቸው።
ሚኒስትሯ በገለጣቸው ወቅት ለ2022 ተይዞ የነበረው 160 ሺህ የባለ ክህሎት ሠራተኞች ቁጥር ጣራ 35 ሺህ ተጨማሪ ቪዛዎችን በማከል ወደ 195 ሺህ ከፍ እንዲል የተደረገ መሆኑን ገልጠዋል።

Home Affairs Minister Clare O’Neil. Credit: AAP / MICK TSIKAS/AAPIMAGE
ተጨማሪው የቪዛ ፈቃድ በእጅጉ አውስትራሊያ የምትሻቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ነርሶች፣ መሐንዲሶችና ሠራተኞች ወደ አውስትራሊያ እንዲመጡ ዕድል ከፋችና ቀውስ ቀናሽ እንደሚሆን አመላክተዋል።