ጠ/ሚ ስኮት ሞሪሰን ለኩክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና የበቁት የተቀናቃኛቸውን 'የሊባኖስ ዝርያነት' አመላክተው እንዳልሆነ አስተባበሉ

*** የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን የዳግም ምርጫ ዘመቻቸውን ጀመሩ፤ ተቀናቃኞቻቸውን እየመሩ ነው።

News

Prime Minister Scott Morrison has rejected allegations he seized on the 'Lebanese background' of his preselection rival in 2007. Source: Getty

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን  ለኩክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ምርጫ ተቀናቃናቸው የነበሩትን ማይክል ቶውከ የሊባኖስ ዝርያ ስላላቸውና ሙስሊም ናቸው ተብሎም ስለሚናፈስ ላይመረጡ ስለሚችሉ በምትካቸው እኔን ምረጡ ብለዋል ለሚለው  ክስ ማስተባበያ ሰጡ። 

በወቅቱ በተደረገው የዕጩ ምርጫ አቶ ቶውክ 82 ድምፅ በማግኘት 8 የድጋፍ ድምፅ ብቻ ያገኙትን አቶ ሞሪሰን በሰፊ አብላጫ ድምፅ አሸንፈዋል።

ሆኖም 22 አመራር አባላት ያሉት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሊብራል ፓርቲ ቅርንጫፍ አቶ ቶውክን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎች ደርሰውኛል በማለት ምርጫው ዳግም እንዲካሔድ ወስኗል። 

በዳግም ምርጫው ወቅትም አቶ ሞሪሰን አብላጫ ድምፅ አግኝተው ለኩክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ለመሆን በቅተዋል።   

ሰሞኑን በ2016 በማይክል ቶውክና ስኮት ቻፕማን የተፈረሙ ሁለት ሕጋዊ ሰነዶች አደባባይ ውለዋል። 

ይህንኑ አስመልክቶ ሳተርዴይ ጋዜጣ አቶ ቻፕማን "ስኮት ሞሪሰን ማይክል ቶውክ ለዕጩነት ከበቃ በአቶ ቶውክ ሊባኖሳዊ ዝርያ ምክንያት 'ኩክ ውስጥ ሊብራል ፓርቲን ትቶ ወደ ሌላ የሚያዘም' ሁነት ይፈጠራል ብለው ነግረውኛል

"እንዲሁም ስብሰባ ላይ ሳለን አቶ ሞሪሰን 'ማይክል ቶውክ እስላም ናቸው' የሚሉ በርካታ ተባራሪ ወሬዎች እንዳሉም ነግረውኛል" ሲሉ ሕጋዊ ሰነድ ላይ ማስፈራቸውን አስነብብቧል። 

አቶ ቶውክም በበኩላቸው በሕጋዊ ሰነዱ ላይ አቶ ሞሪሰን ለሊብራል ቅርንጫፍ ፓርቲ አመራር አባላት የቤተሰቤ ዝርያ ከሊባኖስ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ኩክ ውስጥ በተለይም ከክሮኑላ ብጥብጥ በኋላ የሊባኖስ ዝርያ ያለው የምክር ቤት ወንበር ሊያገኝ እንደማይችል መናገራቸውን እንዳሰፈሩም ጋዜጣው አክሎ ጠቅሷል።  

አቶ ማይክል የሊባኖስ ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ፤ ሃይማኖታቸው የማሮናይት ካቶሊክ ነው። 

አቶ ሞሪሰን አቶ ቶውክ በሊባኖስ ዝርያነታቸውና በሃይማኖታቸው ሳቢያ እንዲገለሉ ቀስቅሰው እንደሁ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ተከታታይ ጥያቄዎች ሶስት ጊዜ በመደጋገም እውነት አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል። 

ባለፈው ማክሰኞ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ "አቶ ሞሪሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ብቃት ያላቸው አይደሉም" ሲሉ ብርቱ ትችት የሰነዘሩት የሊብራል ፓርቲ ሴናተር ኮንቺታ ፌይራቫንቲ-ዌልስ "ሞሪሰንና የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሊብራል ፓርቲ ሽርካዎቻቸው አንድ ማለፊያ ወጣት ሰው አሰናክለዋል። እኔና [የቀድሞው የሊብራል ፓርቲ ምክር ቤት አባል ዲቪ] ክላርክ ሞሪሰንን ለኩክ ተወካይ እንዲሆኑ የተስማማንበት ቀን ይፀፅተኛል" ብለዋል። 

አያዘውም፤ አቶ ሞሪሰን እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይና ከመስመር ያለፈ ጫና በሰዎች ላይ የሚያሳድሩ ስለመሆናቸውም ተናግረዋል።

የሊብራል ሴናተሯን አተያይ ተከትሎ የዋን ኔሽን እና የግል የታዝማኒያ ተወካይ ሴናተር ጃኪ ላምቢ አቶ ሞሪሰንን ሰዎች ላይ ከመስመር ያለፈ ጫና አሳዳሪ ናቸው ሲሉ ድጋፋቸውንና ግለ ተሞክሯቸን ገልጠዋል። 

የሌበር ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ይህንኑ አስመልክተው "ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕሪይ ሌሎች ሰዎች አተያያቸውን እንዲሰነዝሩበትና የራሳቸውንም ብይን እንዲያደርጉ እተዋለሁ" ብለዋል። 

ቀደም ሲልም አቶ አልባኒዚ የሌበር ሴናተር ኪቺንግ በባልደረቦቻቸው ፔኒ ዎንግ፣ ክሪስቲና ኬኔሊና ካቲ ጋለኸር ከመስመር ያለፈ ጫና አድርገውባቸዋል በሚል ጫና አድሮባቸው ነበር። ሆኖም ሶስቱም የሌበር ሴናተሮች አስተባበለዋል። 

 

የፈረንሳይ ምርጫ

የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን የዳግም ምርጫ የመጀመሪያ ግዙፍ የምረጡኝ ዘመቻችውን ባለፈው ቅዳሜ ጀመረዋል።

ከግራና ከቀኝ ክንፎች ይልቅ ማዕከላዊ አቋም ያላቸው አቶ ማክሮን ተቀናቃኛቸውን የአክራሪ ቀኝ ክንፍ መሪ ሜሪን ለ ፔን እና ሌሎች ተፎካካሪዎቻቸውን በስፋት እየመሩ ነው።  

በዩክሬይንና የሩስያ ጦርነትን በመሸምገል መሪ ሥፍራ ይዘው ያሉት ማክሮን ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ያለውን የምግብና የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው በበጋው ወራት እስከ 6,000 ዩሮ ከግብር ነፃ ድጎማ እንዲያከናውኑ የሚያደርጉ መሆኑን ቃል ገብተዋል። 

አክለውም፤ ዝቅተኛ የጡረተኞች አበል ክፍያን ወደ 1,100 ዩሮ በወር ከፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። 


3 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now