በፐርዝ ሰሜናዊ ምሥራቅ 71 ያህል ቤቶች በደን ቃጠሎ ጋዩ

*** ቪክቶርያ የኮሮናቫይረስ ጥቃት ሳታስመዘግብ 28 ተከታታይ ቀናትን አስቆጠረች

Amharic News 03 February 2021

Perth'de yüzlerce itfaiyeci orman yangınlarını kontrol altına almaya çalışıyor. Source: DFES

በፐርዝ ሰሜናዊ ምሥራቅ ክፍለ ከተሞች 71 ያህል ቤቶች በደን ቃጠሎ ጋይተዋል።

የውሮሉ አሳት የተነሳው ሰኞ ፌብሪዋሪ 1 ሲሆን ከ 8,000 ሔክታር መሬት በላይ አንድዷል።

የአካባቢው ባለ ስልጣናት እንደገለጹት ከሆነ ምንም እንኳ ትናንት ማምሻውን የአሳት አደጋ ተከላካዮች ብርቱ የቃጠሎ ሁኔታ ባይገጥማቸውም ተከስቶ ያለው ሁኔታ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ለሚያደርጉት እሳት የማጥፋት ተግባር እምብዛም አጋዥ አይደለም።

የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አግለግሎቶች ኮሚሽነር ዳረን ክሌም እስካሁን አንድም የሰው ሕይወት እንዳልጠፋ ገልጠው፤ ሆኖም ተጨማሪ ንብረቶች ሊወድሙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

 

ቫይረስ ቪክቶሪያ

 

 

ቪክቶሪያ አንዳችም የማኅበረሰብ አባል በኮሮናቫይረስ ሳይጠቃ 28 ተከታታይ ቀናትን አስቆጥራለች፡፡

የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ ይህ ቫይረሱ ከማሕበረሰቡ ውስጥ የተከላበት ቀን በመሆኑ ሁነኛ ቀን እንደሆነ ተናግረዋል።

ይሁንና ጊዜው ቸል መባያ አለመሆኑንንም ልብ አሰኝተዋል።

 ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን አንዳች ግዙፍ ለውጥ ካልተከሰተ በስተቀር በሚቀጥለው ሳምንት ፌብሪዋሪ 12 ላይ ተጥለው ያሉ ገደቦችን እንደሚያላሉ አስታውቀዋል።

 ኒው ሳዝ ዌይልስ አንዳችም የማኅበረሰብ አባል በኮሮናቫይረስ ሳይጠቃ 17 ተከታታይ ቀናትን አስቆጥራለች፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

                                                       


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now