የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ዶሚኒክ ፒሮቴይ ለግማሽ ሚሊየን ነዋሪዎች ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዛትና ማስጠንቀቂያዎች መሰጠቱን አስታወቁ።
በአሁኑ ወቅት 76 ትዕዛዝዞች ለ 200,000 ሰዎች ቀዬአቸውን ለቅቀው እንዲወጡ፤ እንዲሁም 18 ማስጠንቀቂያዎች 300,000 ለሚደርሱ ሰዎች ተሰጥቷል።
በከባድ ዝናብ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ የምዕራብ ሲድኒ ነዋሪዎች ቀዬዎቻቸውን ለቅቀው ወጥተዋል።
የሆክስባሪ፣ ናፒአንና ጆርጅ ሪቨርስ 600 ጊጋ ሊትር ውኃ ፍሰት በዋራጋምባ ግድብ ላይ ረቡዕ ማርች 2 ምሽት ላይ ሞልቶ ፈስሷል።
በመጪዎቹ ሰዓታት 250 ሚሊ ሜትር ዝናብ ሲድኒ፣ ኒውካስል፣ ማዕከላዊ ኮስትና ኢላዋራ ላይ ይዘንባል ተብሎ ይጠበቃል።
በመላው ኒው ሳውዝ ዌይልስ በጎርፍ መጥለቅለቅና የመንገድ መዘጋት ሳቢያ ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።
በጎርፍ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር አምስት ደርሷል።
ኩዊንስላንድ
በደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድም ከባድ ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ተጠቁሟል።
የሜትሮሎጂ ቢሮ በተወሰኑ አካባቢዎች ከ150 ሚሊ ሜትር በላይ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።
እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው እርዳታን የሚሻ ከሆነ ወደ Lifeline በ 13 11 14 ይደውሉ።
ምዕራብ አውስትራሊያ
ምዕራብ አውስትራሊያ ከዛሬ ማርች 3 አንስታ ወሰኖቿን ከፍታለች።
ክፍለ አገሪቷ ሶስት ዙር ክትባት የተከተቡ የተከተቡ መንገደኞችን እንደምትቀበልና እዚያም እንደደረሱ የፈጣን አንቲጄን ምርመራ ማካሔድ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቃለች።
ምርመራ የማካሄዱ ሂደት ቢያንስ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ክለሳ ይደረግበታል።
ክትባቶችን ያልተከተቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት የሆቴል ወሸባ የመግባት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

