የምክር ቤት ወንበራቸውን ያጡት የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን ድል መነሳታቸውን አስታወቁ

የሊብራል ፓርቲ አዲስ መሪ እያፈላለገ ነው

Dutton.png

Outgoing Opposition leader Peter Dutton. Credit: AAP / Mick Tsikas

ተሰናባቹ የዲክሰን ፌዴራል ምክር ቤት አባል፣ የሊብራልና የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን ምንም እንኳ ለ2025 የፌዴራል ምርጫ ለድል አድራጊነት ተስፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም ድል መነሳታቸው አምነው ተቀብለዋል።

 አቶ ዳተን "በእዚህ ምርጫ በመልካም አልተወጣንም፤ ለእዚያም ዛሬ ምሽት ሙሉ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ። ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድ ስለ ዛሬ ምሽቱ ስኬታማነታቸው እንኳን ደስ አለዎት ለማለት ደውያለሁ። ለሌበር ታሪካዊ ወቅት ነው፤ ለእዚያም ዕውቅናችንን እንቸራለን" ብለዋል።

አክለውም ተቀናቃኛቸውና ድል ነስተው የምክር ቤት ወንበራቸውን የተረከቧቸው የሌበር ዕጩ አሊ ፍራንስ ዘንድም ደውለው እንኳን ደስ ያለዎት ማለታቸውንና ወ/ሮ ፍራንስ ማለፊያ ሥራን እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ፍራንስ ለ24 ዓመታት የዲክሰንን ምክር ቤት ይዘው ቆይተው የነበሩትን ፒተር ዳተንን ለማሸነፍ የበቁት ለሶስተኛ ጊዜ ባደረጉት ጥረት ነው።

የሊብራል ፓርቲ ተሰናባቹን የፓርቲ መሪ ፒተር ዳተንን ለመተካት አዲስ መሪ ማፈላለግ መጀመሩንና አንገስ ቴይለርና አንድሩ ሄስቲ ስም ለጊዜው የተጠቀሰ ሲሆን፤ በቀጣይ ቀናት ውስጥ ይፋ የሚሆን ይሆናል።
 

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የምክር ቤት ወንበራቸውን ያጡት የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን ድል መነሳታቸውን አስታወቁ | SBS Amharic