በመላ አውስትራሊያ የፌዴራል 2025 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮችን ድምፅ መቀበል አቁመው ተዘግተዋል።
የድምፅ ቆጠራው ተጀምሯል።
ከ50 ፐርሰንት በታች ይፋ የሆነውን የድምፅ ቆጠራ ተከትሎ የሌበር ፓርቲ የምርጫውን ሂደት በአሸናፊት በማጠናቀቅ መልሶ ቀጣይ የፌዴራል መንግሥት እንደሚያቆምና አንቶኒ አልባኒዚም በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።
ከፓርቲያቸው ድል መነሳት አልፎ የተቃዋሚ ቡድን መሪው ፒተር ዳተን የኩዊንስላንድ ዲክሰን የምክር ቤት ወንበር በሌበር ፓርቲ ዕጩ አሊ ፍራንስ ተወስዷል።