በቤቶች ጉዳዮችና ቤት አልባነት ቃል አቀባይ ማክስ ሻንድለር ማትኸር ተይዞ የነበረው የአውስትራሊያ ግሪንስ ፓርቲ የግሪፊዝ ምክር ቤት ወንበርን እንደሚያጡ የሬድብሪድጅ ቡድን ዳይሬክተር ሳይመን ዌልሽ ተናግረዋል።
በግሪንስ ፓርቲ መሪ አዳም ባንድት ተይዞ ያለው የሜልበርን ከተማ ምክር ቤት እንዲሁ በግሪንስ ፓርቲ ስር መቆየትና አለመቆየት ለጥርጣሬ መዳረጉን የአክሰንት ምርምር ዋና ኃላፊ ሾን ራትክሊፍ አመላክተዋል።
እንዲሁም በግሪንስ ፓርቲ ስቴፈን ቤትስ ተይዞ የነበረው ወደ ሌበር ማዶና ጃሬት እንደሚሸጋገር ይጠበቃል።
የግሪንስ መሪ ባንድት ቀደም ሲል የሜልበርን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የግሪንስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወንበሮችን ይዞ እንደሚቆይና ሁለቱን የብሪስበን የምክር ቤት ወንበሮች ፓርቲያቸው ሊያጣ እንደሚችል ተናግረው ነበር።
ይሁንና የግሪንስ ፓርቲ ዕጩ ሳማንታ ራትማን የሜልበርን ዊልስ የምክር ቤት ወንበርን ከሌበር ፒትር ካሂል ሊወስዱ እንደሚችል ተስፋ መኖሩን፤ ራትክሊፍ አመላክተዋል።
በተጨማሪም የግሪንስ ፓርቲ ኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ የሪችመንድን እንዲሁም የብሪስበን ራያን የምክር ቤት ወንበሮችን የማግኘት ዕድሎች እንዳሉት ተነግሯል።