SKIP TO MAIN CONTENT

ቪክቶሪያውያን ከኖቬምበር 23 ጀምሮ ወደ ኒው ሳውዝ ዌይልስ መጓዝ ይችላሉ

*** ቪክቶሪያ ውስጥ ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በኮሮናቫይረስ የተያዙና የሞቱ ሰዎች አልተመዘገበም

NSW Premier Gladys Berejiklian
NSW Premier Gladys Berejiklian Source: AAP

1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፕሪሚየር ግላዲስ በርጂክሊያን ቪክቶሪያ ላይ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ተጥሎ የነበረው የወሰን ገድብ ከኖቬምበር 23 ጀምሮ እንደሚነሳ አስታወቁ።

ቪክቶሪያ ላይ ለአንድ ወር ተጥሎ ቆይቶ የነበረው ደረጃ አራት የኮረናቫይረስ ገደቦችን አክሎ ከአራት ወራት በላይ የኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ ወሰኖች ተዘግተው ቆይተዋል።

ፕሪሚየር በርጂክሊያን ቪክቶሪያን ጨምሮ ከመላው አውስትራሊያ ወደ ኒው ሳውዝ ዌይልስ የሚመጡት ጎብኚዎች ሁሉ በመልካም ሁኔታ እንደሚያስተናገዱ ገልጠዋል። 

 በሌላም በኩል ቪክቶሪያ ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ ወይም ያለፈ ሕይወት አልተመዘገበም።

ባለፉት14 ቀናት ቪክቶሪያ ውስጥ የቫይረሱ ተዛማችነት 1.7 ሲሆን ምንጫቸው ያልለየ 2 ተመዝግቧል።   

 

 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now