SKIP TO MAIN CONTENT

ድሬዳዋ ቀፊራ አካባቢ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች እንዲወገዱ ከተደረጉበት ጉድጓድ ቆፍረው በማውጣት ሊሸጡ የነበሩ 17 ግለሰቦች በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከተለያዩ ሱቆች ተሰብስበው ተቀብረው የነበሩት የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች 1ሺ700 ሊትር የምግብ ዘይት፣ ዱቄት ወተት እና ሩዝ እንደነበሩ ተገልጧል።

Expired goods.png
Credit: Supplied

1 min read

Published

Updated

By Stringer Report

Source: SBS


Skip to article content

የመጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው ምርቶች እንዲወገዱ ከተደረጉበት ጉድጓድድ ቆፍረው በማውጣት ለመሸጥ በመዘጋጀት ላይ የነበሩ 17 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ድሬ ፖሊስ ገለፀ።

በከተማዋ ቀፊራ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉና የአገልግሎት ግዜ ያለፈባቸው ምርቶች ከተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆች 1ሺ700 ሊትር የምግብ ዘይት፣ ዱቄት ወተት እና ሩዝ ተለይቶ በመሰብሰብ በጉድጓድ ተቆፍሮ እንዲወገድ መደረጉን የገለፀው ፖሊስ ተከሳሾቹ ምርቱ ከተቀበረበት ጉድጓድ ቆፍረው በማውጣት ለመሸጥ በመዘጋጀት ላይ እንዳሉ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት መያዛቸውን አስታውቋል።

የአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያና የመጋላ ፖሊስ ጣቢያ በጋራ በሰሩት ቅንጅታዊ ስራ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው 10 ሴት እና 7 ወንድተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጧል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now