የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን የሥራ ኃላፊነት ምደባ ይፋ ሆነ

*** 10 ሴቶች የተቃዋሚ ቡድን ካቢኔ ውስጥ ተመድበዋል።

News

Source: AAP

የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን ከ24 የካቢኔ አባላት ውስጥ 10 ሴቶችን ማከላቸውንና ሌሎች የሥራ ኃላፊነት ምደባዎችን አስታወቁ። 

በተቃዋሚ ቡድን ካቢኔ ውስጥ ከሊብራል ፓርቲ ወገን ከተካተቱት ውስጥ፤

  • ጄን ሂዩም - ፋይናንስ
  • ሳራ ሄንደርሰን - ኮሙኑኒኬሽን
  • ካረን አንድሩስ - የአገር ውስጥ ጉዳዮች
  • አን ራስተን የጤና አረጋውያን ክብካቤ ቃል አቀባዮች ሆነዋል።

አለን ታዥ የትምህርት፣ አንገስ ቴይለር የዐቃቤ ንዋይ ጉዳይች፣ አንድሩ ሄስቲ የመከላከያ ቃል አቀባይ ሆነዋል። 

በሌላ ወገን የናሽናልስ ፓርቲ ስድስት የካቢኔ መደቦችን ወስዷል።

አዲሱ የናሽናልስ ፓርቲ መሪና የተቃዋሚ ቡድን ምክትል መሪ ዲቪድ ሊትልፕራውድ የእርሻ፣ የናሽናልስ ምክትል መሪ ሴናተር ፔሪን ዴቪ የውኃ ሃብቶችና የድንገተኛ አስተዳደር፣ ሴናተር ብሪጂት ማኬንዚ የመሠረተ ልማት፣ ትራንስፖርትና ሪጂናል ልማት፣ ሴናተር ሱዛን ማክዶናልድ፣ የሃብት ምንጮችና የሰሜናዊ አውስትራሊያ፣ ኬቨን ሆጋን የንግድና ቱሪዝም፣ የቀድሞው የናሽናልስ መሪና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ የጡረተኛ ወታደሮች ጉዳዮች ቃል አቀባዮች ሆነው ተመድበዋል። 

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now