በዓለም ዝነኛ የነበረው የእግር ኳስ ተጫዋች አጀንቲናዊው ዲያጎ ማራዶና ለብሶት የነበረው የብሔራዊ ቡድን ጀርሲ በጨረታ $12.5 ሚሊየን የአውስትራሊያ ዶላር ተሸጠ።
ማራዶና ኖቬምበር 2020 ከዚህ ዓለም በ60 ዓመቱ በሞት የተለየ ሲሆን፤ ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን 10 ቁጥር ለብሶ በ1986 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ከእንግሊዝና ሜክሲኮ ጋር ተጫውቷል።
በእኒዚያ ግጥሚያዎች ወቅትም በዓለም የእግር ኳስ ታሪክ ዝነኛ የሆኑ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።
አንደኛዋን ግብ ያስገባው በአርጀንቲናና እንግሊዝ መካከል በተደረገው ግጥሚያ የሁለተኛው ግማሽ ጨዋታ ሊፈፀም ስድስት ደቂቃዎች ሲቀሩ በእጁ ነክቶ ያስገባት ግብና እስካሁንም ድረስ "የእግዚአብሔር እጅ" በሚል የምትታወሳዋና አወዛጋቢዋ ግብ ናት።

ማራዶና ምንም እንኳ በእጁ ነክቶ ግቧን ቢያስቆጥርም በወቅቱ ዳኛው ልብ ብሎ ስላልተመለከተና እንደ ዛሬው የቪዲዮረዳት ዳኛ ቴክኖሎጂ ባለመኖሩ በግብነት ፀድቃ አርጀንቲና እንግሊዝን 1 ለ 0 መምራት ችላለች።
ቀጥሎም ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ሌላ "የክፍለ ዘመኑ ግብ" የተሰኘት ግብ በማስቆጠሩ አርጀንቲና እንግሊዝን 2 ለ 1 እንድትረታ አብቅቷል።

ጫት ሳዑዲ አረቢያ
የሳዑዲ ባለስልጣናት በትናንትናው ዕለት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ አገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች የዘለቀ 45.6 ቶን ጫትና 760 ኪሎ ግራም ሃሺሽ በድንበር የፀጥታ ኃይላት ቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።
የድንበር ፀጥታ ኃይላቱ ከጫትና የአደንዛዥ ዕፆቹ ጋር ተያይዞ 41 የሳዑዲ ዜጎችን፣ 11 ኢትዮጵያውያን፣ ሰባት የመናውያንና ሁለት የፓኪስታን ዜጎች ለእሥር መዳረጋቸውን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጧል።
ቀደም ሲልም ኤፕሪል 8 ወደ ሳዑዲ ዘልቆ የገባ 39 ቶን ጫት መያዙም ተጠቅሷል።

