ጆሴፍ ዊልያምስ - የቀድሞው የኩክ አይላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው ኦክላንድ - ኒውዝላንድ ውስጥ አልፏል።
የሕክምና ማኅበረሰብ ሁነኛ አባል የነበሩት የ82 ዓመቱ ዶ/ር ዊልያምስ ኦክላንድ ከተማ ሆስፒታል ውስጥ ለሕክምና የገቡት ኦገስት 13 ሲሆን ትናንት ዓርብ ሴፕቴምበር 04 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የዶ/ር ዊልያምስን ሞትና የኮቪድ-19 ገዳይነትን አስመልክተው የኒውዝላንድ የጤና ዋና ዳይሬክተር አሽሌይ ብሉምፊልድ ሲናገሩ " የዛሬው ዜና አሳዛኝ ነው። ዳግም ኮቪድ-19ን ችላ ሳንል ንቁ ሆነን የመጠንቀቁን ጠቀሜታ ልብ የሚያሰኘን ነው" ብለዋል።
ዶ/ር ዊልያምስ ለመጀመሪያ ጊዜ የኩክ አይላንድስ ፓርላማ አባል ሆነው የተመረጡት በ1968 ሲሆን ከ1974 እስከ 1978 የጤናና የትምህርት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ከጁላይ እስከ ኖቬምበር የኩክ አይላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ።
እንዲሁም፤ ከ1995 እስከ 1997 የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ የቦርድ አባል በመሆን ሠርተዋል።
ቫይረስ - የተቃውሞ ሰልፍ
በሜልበር ከተማ መታሰቢያ አካባቢ 300 ያህል ሰዎች ጭምብል የማጥለቅና ሰዓት ዕላፊን ጨምሮ ሜልበርን ውስጥ ተጥለው ያሉትን የኮሮናቫይረስ ገደቦች በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን አንድ የፖሊስ ሠራዊት አባልም በቡጢ ተመትቷል።
ከተቃውሞ ሰልፈኞች ውስጥ "ወረርሽኝ የሚባል የለም - የመንግሥት አምባገነንነት እንጂ" የሚልና ሌሎችም ፀረ-መንግሥት መፈክሮች ይዘው ተገኝተዋል። የአውስትራሊያ ሕዝብ መዝሙርንም ዘምረዋል።

Victoria Police arrest and put a face mask on a protester outside of the Shrine of Remembrance in Melbourne. Source: AAP
ፖሊስ በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፍ ሜልበርን ውስጥ ለማካሔድ ውጥን መኖሩን ነቅቶ ይጠብቅ የነበረ ሲሆን የቪክቶሪያ ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ሉክ ኮርኒሊየስ የቪክቶሪያ ፖሊስ ከአንድ ሳምንት በፊት ለተቃውሞ ሰልፈኞቹ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር አስታውቀዋል።

4 September: Victoria police defend arrest of anti-lockdown organiser despite 'the optics' Source: SBS
አያይዘውም " ' ሉዓላዊ ዜጎች' በሚል የራሳቸውን እዚህ ግባ የማይባል ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን፣ 5G የልጅ ልጆቻችሁን ይገድላል የሚሉ አተያዮችን ይዘው የወቅቱን ሁኔታ ተጠቅመው ተፅዕኖ ለማሳደር በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚያወሩ ናቸው" ብለዋል።
ሰልፈኞቹ የተቃውሞ ድምጻቸውን በሚያሰሙበት ወቅት ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ መግለጫ ይሰጡ የነበሩት ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ "ይህ ብልህነት፣ ይህ ደህንነትን ጥበቃ፣ ይህ ሕጋዊነትም አይደለም። እንደ እውነቱ ከሆነ ውጪ ወጥቶ ተቃውሞ ማድረጉ ራስ ወዳድነት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ 76 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል፤ 11 ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በመላው አውስትራሊያ 748 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን 661ዱ ከቪክቶሪያ ናቸው።
ነገ አሑድ ፕሪሚየር አንድሩስ ሜልበርን ላይ ተጥለው ያሉት የደረጃ 4 ገደቦችና ሪጂናል ቪክቶሪያ ተጥለው ያሉት ደረጃ ሶስት ገደቦች የሚላሉበትን የሁለትዮሽ ፍኖተ ካርታዎች ይፋ ያደርጋሉ።
Share

