ከ2.1 ሚሊየን በላይ አውስትራሊያውያን የኮቪድ-19 ሶስተኛ ዙር ክትባት አለመከተባቸው ተገለጠ

***የታዝማኒያ ምክትል ፕሪሚየር ጀርሚ ሮክሊፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የታዝማኒያ ፕሪሚየር ሆነው ቃለ መሃላ ሊፈጽሙ ነው።

COVID-19 update

Australia has brought forward implementing third-dose booster shots for Covid-19 as the nation battles outbreaks of the omicron variant. Source: Getty

አንድ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ኮሚቴ "በብዥታና ቸልተኝነት" ሳቢያ ከ2.1 ሚሊየን በላይ አውስትራሊያውያን የኮቪድ-19 ሶስተኛ ዙር ክትባት ያለመከተባቸውን ሪፖርት አደመጠ። 

የፌዴራል ክትባት ስርጭት ዋና ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ፍሬዌን ኮሚቴው ፊት ቀርበው 11 ፐርሰንት ያህል ለተጨማሪ ክትባት መመዘኛ ብቁ የሆኑ ግለሰቦች የሶስተኛ ዙር ክትባታቸውን አለመከተባቸውን ተናግረዋል። 

ጄኔራሉ የሶስተኛውን ዙር ክትባት ካልተከተቡት ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች የሆኑ ግለሰቦች መሆናቸውንም አክለው ገልጠዋል። 

ታዝማኒያ ፕሪሚየር

የታዝማኒያ ምክትል ፕሪሚየር ጀርሚ ሮክሊፍ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የታዝማኒያ ፕሪሚየር ሆነው ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል።

በዚህ ሳምንት መጅመሪያ ሰኞ ዕለት ፕሪሚየር ፒተር ጋትዊን በፍቃዳቸው ከታዝማኒያ ፕሪሚየርነትና የባስ ምክር ቤት አባልነታቸውን በፈቃዳቸው ለቅቀዋል።

News
Tasmania Deputy Premier Jeremy Rockliff (L). Source: Getty

በፕሪሚየር ጋትዊን እግር ለመተካት እስካሁን ፈቃደኝነታቸውን የገለጡት ከ2014 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በምክትል ፕሪሚየርነት ያገለገሉት አቶ ሮክሊፍ ብቻ ናቸው። 

በእሳቸው ምትክ ምክትል ፕሪሚየር ለመሆን የትራንስፖርት ሚኒስትር ማይክል ፈርጉሰንና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ኢሊስ አርቸር እንደሚፎካከሩ ተነግሯል።  

 


1 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now