ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክትላቸው "ግብዝ" እና "ዋሾ" በመባላቸው ፖለቲካ "ጭካኔ" የተመላበት መስክ ነው አሉ

*** የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ ወደብ ድልድይ ላይ በቋሚነት ሊውለበለብ ነው

News

Demonstrators have called for the Australian Aboriginal Flag to be flown atop Sydney Harbour Bridge for years. Source: AAP

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ "ግብዝ" እና "ዋሾ" መባላቸውን አስመልክተው ፖለቲካ "ጭካኔ" የተላበሰ የሥራ መስከ መሆኑን ተናገሩ። 

አቶ ጆይስ ለአፍ ወለምታቸው ይቅርታ ጠይቀዋል፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሥራ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለመነሳትም የሥራ መልቀቂያ አስገብተዋል። 

ይቅርታቸው በአቶ ሞሪሰን ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን፤ የሥራ ኃላፊነታቸውን የመልቀቁ ጥያቄ ግና ተቀባይነት ባለማግኘቱ በሥራቸው ፀንተው ይቀጥላሉ።   

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጆይስ ጋር ባለፉት ጊዜያት የቅርብ የሥራ ግንኙነት እንደነበራቸው አውስተው ለወደፊቱም በዚያው መልክ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። 

አክለውም፤ ሰውን በቁጣውና ምሬቱ እንደማይመዝኑ ተናግረዋል። 

 የነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ ወደብ ድልድይ ላይ "በተቻለ ፍጥነት" በቋሚነት እንዲውለበለብ እንደሚደርግ ፕሪሚየር ዶሚኒክ ፔሮቴይ አስታወቁ። .

በዕርቅ ማሳያነት ዕሳቤውን ዕውን ለማድረግ ዘለግ ላሉ ጊዜያት ጥረት መደረጉን የገለጡት ፔሮቴይ "አስፈላጊ ከሆነ እኔ ራሴ ድልድዩ አናት ላይ ወጥቼ ሰንደቅ ዓላማውን እሰቅላለሁ" ብለዋል። 

የፌዴራል መንግሥቱ የሰንደቅ ዓላማውን የቅጂ መብት ከአርቲስትና አንቂ ሃሮልድ ቶማስ በ$20 ሚሊየን ዶላርስ ወጪ ወደ ራሱ አስተላልፏል።

አቶ ቶማስ ሰንደቅ ዓላማን የነደፉት በ1971 ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተውለበለበውም በዚያ ዓመት በተካሔደው የአደላይድ ብሔራዊ ነባር ዜጎች ቀን ነው። 

 

 


1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now