የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት 801 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ

የ2016 በጀት ለፌደራል መንግሥት መደበኛ ወጪዎች 369.6 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.9 ቢሊዮን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214.07 ቢሊዮን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊዮን በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል።

Council of Ministers.jpg

The Ethiopian Council of Ministers. Credit: CoM

ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 29 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ21ኛ መደበኛ ስብሰባው የ2016 ረቂቅ በጀትን አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው ስብሰባ የፌዴራል መንግስት የተለያዩ የልማት እቅዶችን፣ የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫዎች አጢኖና የደህንነት ጉዳዮች ተመልክቶ የሚቀጥለው ዓመት በጀት መዘጋጀቱ ተነግሯል።

"[የ2016 በጀት] በአሥር ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ የተቀመጡ ግቦችን ታሳቢ በማድረግ፣ የሀገር ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በህግ ማስከበር ዘመቻው የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ሽግግርን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ የተቃኘ" ሲል ስለ ረቂቅ በጀቱ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ከዚህ ባሻገርም በጀቱ የ2016 እስከ 2020 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊሲካል ማዕቀፍን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው ተብሏል።

የ2016 በጀት ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች 369.6 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203.9 ቢሊዮን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214.07 ቢሊዮን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊዮን በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል።

ምክር ቤቱ በቀረበው በጀት ላይ ተወያይቶ 'ግብዓቶችን በማከል' ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

ከ2015 በጀት ጋር ሲነጻጸር 15 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚበልጠው ረቂቅ በጀቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል፡፡

ሰኔ 30 የሚጠናቀቀው የ2015 ዓመት በጀት 786.6 ቢሊዮን ብር ነው።



Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service