ፕሬዚደንት ፑቲን ምዕራባውያን በዩክሬይን አየር ላይ የበረራ እገዳ ቢያደርጉ ሩስያ በጦርነት እወጃ እንደምትወስደው አሳሰቡ

*** በጎርፍ አደጋ ሳቢያ ኩዊንስላንድና ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 17 ደረሰ።

News

refighters try to extinguish a fire at a house in Chernihiv, Ukraine, as Russia's invasion entered its 10th day. Source: Getty

የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን የአየር ድንበር ላይ የበረራ እገዳ የጦርነት እወጃ ሊሆን እንደሚችል አሳሰቡ።

የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የሰሜን አትላንቲክ የጋራ ቃልኪዳን ድርጅት በዩክሬይን የአየር ድንበር ላይ የበረራ እገዳ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ይሁንና የቃል ኪዳኑ ድርጅት ዋና ኃላፊ ጄንስ ሶልተንበርግ የዩክሬይንን ጥያቄ እንደሚረዱ ገልጠው፤ እንዲህ ያለው እርምጃ ግና የሩስያን አውሮፕላኖች መትቶ ከመጣል ጋር ስለሚያያዝ አውሮፓን ወደ ሙሉ ጦርነት የሚያመራ መሆኑን ልብ አሰኝተዋል። 

ፕሬዚደንት ፑቲን የዩክሬይን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት አባል መሆን መዘዞች እንዳሉት አስጠንቀቅው፤ ሩስያ ላይ አስቸኳይ ጊዜያዊ አዋጅ ለመደንገግ ዕቅድ የሌላቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።  

አቶ ፑቲን የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ የቃል ኪዳኑ ድርጅት በግጭቱ ውስጥ ሊሳተ ፍ እንደሚችል የተናገሩትን አንስተውም "ኃላፊነት የጎደለው አባባል" ሲሉ ተችተዋል።  

በሌላ በኩል የሩስያ መከላከያ ባለስልጣናት የዩክሬይን ማሪዩፖል እና ቮልኖቫክሃ ከተሞች ላይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጊዜ ያበቃ መሆኑን አስታውቀዋል።

እንዲሁም ግዙፉ የሩስያ አየር መንገድ ኤሮፍሎት ዓለም አቀፍ በረራዎቹን ከቤላሩስ በስተቀር ከማርች 8 ጀምሮ እንደሚያቆም ገልጧል።   

የሩስያ አቬይሽን ኤጄንሲ ሮዛቪያትስያ ሁሉንም የሩስያን የውጭ ኪራይ አውሮፕላኖችን ጨምሮ የመንገደኞችና የጭነት አውሮፕላኖች በሙሉ ከባሕር ማዶ በረራዎችን እንዲገቱ ወስኗል። 

 ዩክሬይን አውስትራሊያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ትናንት ማምሻውን ከዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ጋር መነጋገራቸውን ገለጡ። 

አቶ ሞሪሰን አውስትራሊያ የሩስያን ወታደራዊ እርምጃ እንደምታወግዝና ከዩክሬይን ጎን መቆሟን ለፕሬዚደንቱ አረጋግጠዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ የአውስትራሊያን ሰብዓዊና ወታደራዊ እገዛ ማድነቃቸውን ጠቁመዋል። 

አቶ ዜሌንስኪ ሩስያ የዩክሬይን ኑክሊየር ተቋማት ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች ስጋት ያሳደረባቸው መሆኑን የገለጡ ሲሆን፤ ሁለቱ መሪዎች አውስትራሊያ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር አብራ እንደምን እገዛዋን ለዩክሬይን እንደምታጠናክር ተወያይተዋል።  

አቶ ሞሪሰን ዩክሬይን የሩስያን ወረራ ተፃርራ "እጅግ አስደማሚ ወኔ" ማሳያቷን አድንቀው ወረራርውን "በመላው አውስትራሊያውያን ስም አወግዛለሁ" ብለዋል። 

                         

ሼን ዋረን

ዝነኛው አውስትራሊያዊ የቀድሞ ክሪኬት ተጫዋች ሼን ዋረን አስከሬን ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ በመሰናዶ ላይ ነው።  

የ52 ዓመቱ የቀድሞው ኮከብ ክሪኬት ተጫዋች ታይላንድ ኮህ ሳሙይ ደሴት ሳለ ሕይወቱ በልብ ድካም ሳቢያ ሳያልፍ እንዳልቀረ ተነግሯል። 

በታይላንድ የአውስትራሊያ አምባሳደር አስከሬኑን ወደ ዋረን መኖሪያ ከተማ ሜልበርን ለመመለስ ከታይላንድ ፖሊስ ጋር በጋራ እየሠሩ ይገኛሉ።

አምባሳደር አላን ማኪነን የታይላንድ ፖሊስ የዋረንን ሞት ተከትሎ ትልቅ ሐዘኔታ የተሰማቸው መሆኑንንም ተናግረዋል።  ምስጋናቸውንም ለታይላንድ ፖሊስ አቅርበዋል። 

የቪክቶሪያና ፌደራል መንግሥቱ በጋራ ለዋረን ቤተሰብ መንግሥታዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን ገልጠዋል። 

 ጎርፍ ኩዊንስላንድና ኒው ሳውዝ ዌይልስ 

ጎልድ ኮስት ውስጥ የአንዲት ሴት አስከሬን መገኘትን ጨምሮ በጎርፍ አደጋ ሳቢያ ኩዊንስላንድና ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 17 ደረሰ። 

አስከሬኑ የተገኘው ትናንት ቅዳሜ ማርች 5 ማድጂርባራ ውስጥ በኩዊንስላንድ ጠላቂ ፖሊስ አባላት ሲሆን፤ ግለሰቧ ለመጨረሻ ጊዜ ፌብሪዋሪ 27 በሕይወት የታዩትና ማክሰኞ ዕለት የደረሱበት ያልታወቀ ተብሎ ሪፖርት የተደረደገው አንዲት የ42 ዓመት ሴት መሆንና አለመሆናቸውን ለማረጋግጥ በፖሊስ በኩል ጥረት እየተደረገ ነው።    

የክፍለ አገራትና ፌዴራል መንግሥታት በጎርፍ አደጋው ለተጎዱ ነዋሪዎች ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን፤ ዛሬ እሑድ ማርች 6 በሁለቱ በጎርፍ መጥለቅለቅ የደረሰባቸው ክፍለ አገራት ውስጥ ከባድ ዝናብ እንደሚዘንብ ይጠበቃል።   

 

 

 

 

 

 

 

 

                                                          

 

 


3 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now