የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ሕወሓት” እና “ሸኔ”ን በሽብርተኝነት ፈረጀ

*** የቻይና - አውስትራሊያ ስትራቴጂካዊ ምጣኔ ሃብት ምክክር መድረክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች

SBS Amharic

Source: SBS Amharic

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሚያዝያ 28, 2013 “ሕወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተመራለት የውሳኔ ሀሳብ ተከትሎ በሙሉ ድምፅ ይሁንታ ቸሯል፡፡

የሚንስትሮች ምክር ቤት  “የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” ድርጅቶች በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ መክሮ የውሳኔ ሐሳቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ እንዲቸረው የመራው ሚያዝያ 23, 2013 ባካሄደው ስብሰባ ነበር።

ድርጅቶቹ በሽብር ወንጀል ተግባራት የሚጠየቁባቸውን አንቀጾች ሲጠቅስም፤

  • ስለዚህ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 መሠረት “ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ወሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል።
  • እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረት በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚ ይሆናል

ብሏል።

 የአውስትራሊ ቻይና የውይይት መድረክ

 

 ቻይና ከአውስትራሊያ ጋር ታካሂድ የነበረውን ቁልፍ የምጣኔ ሃብት የንግግር መድረክ ላልተወሰነ ጊዜ ገታች። ይህም እርምጃዋ ከቪክቶሪያ ስቴት ጋር አድርጋው የነበረው የሐር መንገድ ፕሮጄክት በፌዴራል መንግሥቱ በወርሃ ማርች በመሰረዙ የወሰደችው የአጸፋ ምላሽ ተደርጎ ተወስዷል።

እርምጃው ማናቸውንም ዋነኛ የምጣኔ ሃብት ማዕቀፍ የሚያግድ፣ ሁሉንም የቻይና - አውስትራሊያ ስትራቴጂካዊ ምጣኔ ሃብት ምክክር መድረክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያቋርጥ ነው። 

ቻይና እርምጃዋን አስመልታ ይፋ ባደረገችው መግለጫዋ የሞሪሰን መንግሥትን "አጨናጋፊ" አተያይ ያለው በማለት ኮንናለች።

የትግራይ አዲስ አስተዳዳሪ 

 

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሰየሙ።

እስካሁን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስትር ዲኤታ በመሆን ተሾመዋል።

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now