ኢትዮጵያን ወክሎ በዓለም ዙሪያ ባሉ ከ200 ሚሊየን በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችና በተለይ በኢትዮጵያ ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ውጪ ያሉ የክርስትና እምነት ተከታዮችን አክሎ በሀገር ውስጥና በበሕር ማዶ ባሉ አማኒያን ዘንድ በደመቀ መንፈሳዊ በዓልነት መከበር ጀምሯል።

ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ቤላሩስ፣ ጆርጂያ፣ ካዛኪስታን፣ ሜሶዶኒያና ሞልዶቫ በዓለ ልደትን ጃኑዋሪ 7 የሚያከብሩ ሲሆን፤ አርሜኒያ ጃኑዋሪ 6፤ ሮማኒያ፣ ቡልጋሪያ፣ ግሪክና ዩክሬይን ዲሴምበር 25 ያከብራሉ።
ካናዳ
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጁስቲን ትሩዶ በውስጣዊ የፖለቲካ ፍትጊያ ከመንበረ ስልጣናቸው ለመልቀቅ መፍቀዳቸውን አስታወቁ።
የሊብራል ፓርቲ ውስጣዊ የፖለቲካ ሽኩቻ ከትሩዶ በፊት የፋይናንስ ሚኒስትራቸውን ከስልጣን መልቀቅ ግድ አሰኝቷል።
የ57 ዓመቱ ትሩዶ በ2015 ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በበቁበት ወቅት "ወርቃማው ልጅ" እስከ መሰኘት በቅተዋል።
ሆኖም የዋጋ ግሽበትና የምግብ ዋጋ ከ30 እስከ 40 ፐርሰንት መጨመር፣ የመኖሪያ ቤት ቀውስ፣ የዶናልድ ትራምፕን የታሪፍ ጭማሪ ዛቻ አክሎ ዓለም አቀፍ የግጭት ጫናዎች የፈጠሯቸው አሉታዊ ክስተቶች ተካትተው በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ወደ 33 ፐርሰንት ማሽቆልቆልን አስከትሎባቸዋል።
ለፍልሚያ አይታክቴነት የሚታወቁት ትሩዶ ከስልጣን እንደሚለቁ ለማስታወቅ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት በይፋ የስሜት መደፍረስ ይታይባቸው ነበር።
ለቀጣዩ ምርጫም ፓርቲያቸውን መርተው ለመፋለም ተመራጩ መሪ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
የካናዳ ፓርላማ ጃኑዋሪ 27 እንደሚሰየም ቀደም ተብሎ ቀን የተቆረጠለት ቢሆንም፤ የሊብራል ፓርቲ ዕጩዎቹን አወዳድሮ መሪውን እስኪመርጥ ድረስ የሚኖረው ጊዜ በቂ ባለመሆኑ የጠቅላይ እንደራሴው ፈቃድ ታክሎበት ለማርች 24 ተዘዋውሯል።

