የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ ለኩባንያው በሞባይል የገንዘብ ዝውውር እንዲያከናውን እንደተፈቀደ ይፋ ሆኗል።
ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፥ “የኬንያ ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ይህን እንዳስፈጽም የቤት ሥራ ሰጥቶኝ ነበር፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን አገልግሎት በመፍቀዱ አመሰግናለሁ” ብለዋል።
የቴክኖሎጂ አብዮት እንደምን ተልምዷዊ ተግዳሮቶችን በመሻገር ዘላቂ ብልፅግናን ማበረከት እንደቻለና ከሳፋሪኮም ስኬት ጋርም እንደምን ተያያዥ እንደሆነ አንስተዋል።
ሳፋሪኮም በኬንያ በኤም ፔሳ የገንዘብ አገልግሎት ያገኘውን ስኬት በኢትዮጵያ ለመድገም እንደሚሠራም አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም የቴሌ ብር አገልግሎት በማስጀመር ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወሳል።