ተመድ ሩስያን ከሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት አገደ፤ ሩስያ ከምክር ቤቱ ራሴን አሰናብቻለሁ አለች

*** የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሴት ልጅ ካሮላይን ኬኔዲ በአውስትራሊያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው ወድ ካንብራ ለመምጣት የምክር ቤት ይሁንታን እየጠበቁ ነው።

News

The board showing the passage of the resolution during a UN General Assembly vote on a draft resolution seeking to suspend Russia from the UN HR Council. Source: Getty

ሩስያን ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ በቀረበው የአቋም መግለጫ ላይ ከ193 የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ሁለት ሶስተኛ የይሁንታ ድምፅ አግኝቶ አልፏል።

ትናንት ኤፕሪል 7, 2022 በተካሔደው የጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ አሰጣጥ ላይ 93 አገራት ይሁንታቸውን ሲቸሩ 24 ተቃውመዋል፤ 58 ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

News
Source: UN

 

ድጋፋቸውን ካሰሙት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ፣ አውስትራሊያና ሶስት የአፍሪካ አገራት ሲገኙበት፤ ተቃውሞ ካሰሙት ውስጥ ሩስያ፣ ቻይናና ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ የአፍሪካ አገራት ይገኙበታል።   

ለእገዳው ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው የሩስያ ጦር ዩክሬይን ውስጥ ፈጽሟቸዋል ከተባሉት የሰላማዊ ሰዎች ግድያዎች ጋር ተያይዞ ነው። 

በሌላ በኩል በተመድ የሩስያ ምክትል ቋሚ ተወካይ ኩዝሚን ሩስያ ዕለቱኑ ምክር ቤቱን ለቅቃ ለመሰናበት መወሰኗን አስታውቀዋል። 

አክለውም፤ ምክር ቤቱ በአንድ የመንግሥታት ቡድን የአጭር ጊዜ ዓላማ በበላይነት የተያዘ እንደሆነ ተናግረዋል።  

የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር

የዩናይትድ ስቴትስ ዕጩ አምባሳደር ዕጩነታቸው ከፀደቀ የአውስትራሊያንና ዩናይትድ ስቴትስን ወዳጅነት ይበልጡን ለማጠናከር ታትረው እንደሚሠሩ አስታወቁ። 

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሴት ልጅ ካሮላይን ኬኔዲ በአውስትራሊያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው ወድ ካንብራ ለመምጣት ዕጩነታቸው ይሁንታ ለማግኘት በሂደት ላይ ይገኛል።

News
Caroline Kennedy speaks at a press conference upon arrival at Narita International Airport on November 15, 2013 in Narita, Chiba, Japan. Source: Getty

ካሮላይን ኬኔዲ ቀደም ሲል በፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በጃፓን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘደንት ሆነው አገልግለዋል።  

ታዝማኒያ ፕሪሚየር

ጀርሚ ሮክሊፍ በሊብራል ፓርቲ ስብሰባ ያለተቀናቃኝ 47ኛው አዲሱ የታዝማኒያ ፕሪሚየር ሆነው በሙሉ ድምፅ ተመረጡ።

News
Tasmanian Deputy Premier Jeremy Rockliff. Source: AAP

አቶ ሮክሊፍ በፕሪሚየርነት ለመመረጥ የበቁት ሰኞ ዕለት ከታዝማኒያ ፕሪሚየርና ባስ የምክር ቤት አባልነታቸው በፈቃዳቸው በለቀቁት ፒተር ጋትዊን ምትክ ነው።  

 

 


2 min read

Published

Updated

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now