SKIP TO MAIN CONTENT

ለኒው ሳውዝ ዌይልስ ተጨማሪ 300,000 ክትባቶች ሊሰጡ ነው፤ የገንዘብ ድጎማም ይደረጋል

*** ኒው ሳውዝ ዌይልስ 38 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል

SBS Amharic
Source: SBS Amharic

1 min read

Published

By NACA

Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Skip to article content

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የኮሮናቫይረስን ለመፋለም ያግዝ ዘንድ ተጨማሪ 300,000 ክትባቶችን ለኒው ሳውዝ ዌይልስ እንደሚልክ አስታወቀ።

ተጨማሪ የሚላኩት የኮሮናቫይረስ ክትባት ዓይነቶች አስትራዜኒካና ፋይዘር ሲሆኑ፤ በቀዳሚነት የሚሰጡትም ለሲኒ የደቡብ ምዕራብ ነዋሪዎች ነው።

ኒው ሳውዝ ዌይልስ ዛሬ ዕለተ ሐሙስ 38 ነዋሪዎቿ በቫይረሱ መጠቃታቸውን አስታውቃለች። ከ38ቱ ውስጥ 18ቱ ራሳቸው አግለልለው የሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት እንደሆኑም ተገልጧል። 

ቀደም ሲል ለሁለት ሳምንታት ተጥሎ የነበረው ገደብ ለሶስተኛ ሳምንት መራዘምን ተክትሎ የፌዴራል መንግሥቱ ጊዜያዊ ድጎማ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን አስታውቀዋል።

Prime Minister Scott Morrison
Prime Minister Scott Morrison at a press conference at Kirribilli House in Sydney, Thursday, July 8, 2021. Source: AAP

ምንም እንኳ ከ $325 - $500 ጊዜያዊ አስቸኳይ ድጎማውን ለመቀበል የሚችሉት ከ$10,000 በታች ተቀማጭ ያላቸው ቢሆንም ከሶስተኛው ሳምንት ጀምሮ ባሉት ታካይ ቀናት የ$10 ሺህ ተቀማጭ ጣራ እንደሚነሳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጠዋል። 

 


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now