የፌስቡክ ወላጅ ኩባንያ ሜታ ከ400 በላይ ኧፖች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ግለሰቦችን ዳታ ለመስረቅ መሠራታቸውን ለግዙፎቹ ኩባንያዎች አፕል እና ጉግል አስታውቋል።
ከእነዚህም ውስጥ የፎቶ አርታኢ፣ ሆሮስኮፕ እና የአካል ማጠንከሪያን የመሳሰሉ በርካታ ኧፖች መሆናቸውን ጠቁሟል።
አፕል እና ጉግል የሜታ ሪፖርት ከደረሳቸው በኋላ የማልዌር አፖችን መክላታቸውን ገልጠዋል።
ሜታ እንዳስታወቀው ከሆነ የፌስቡክ ዳታዎ በሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎች ከተጠለፈ ጠላፊዎቹ ለጓደኞችዎ የሚልኳቸውንና የሚቀበሏቸውን መረጃዎች ጨምሮ ሙሉ በሙሉ አካውንትዎን በቁጥጥራቸው ስር ማድረግ ይችላሉ።
በእርስዎ ስም መልዕክቶችን መላክና መቀበል ይቻላቸዋል።
ምን ማድረግ ይችላሉ?
- አዲስ ኧፕ ከመጫንዎ በፊት ትክክለኛ ስለመሆኑ ያጣሩ።
- የጫኑት ኧፕ ለዳታ ስርቆት የዳረገዎት ከሆነ ያስወግዱትና በአዲስ የይለፍ ቃል (password) ይተኩ።
- ተመሳሳይ የይለፍ ቃል ለተለያዩ ድረ ገፆች አይጠቀሙ።
- የሁለት ዙር ማንነት ማጣሪያን ይጠቀሙ።
.